የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የግብርና ልማት ኢኒሼቲቮች የአርሶ አደሩን ሕይወት እየቀየሩ ነው

Nov 26, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሮቤ፣ ህዳር 17/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን እየተተገበሩ ያሉ የግብርና ልማት ኢኒሼቲቮች የአርሶ አደሩን ምርታማነትና ገቢ በማሳደግ የኑሮ ሁኔታውን እየቀየሩ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ።

በዞኑ እየተከናወኑ ካሉት የግብርና ልማት ኢኒሼቲቮች መካከል የአትክልትና ፍራፍሬ፣ የማር ምርት፣ የከብትና የዶሮ እርባታ፣ የበጋ ስንዴና የወተት ልማት ይገኙበታል።

የልማት ኢኒሼቲቮቹ አርሶ አደሩ ከመደበኛ የእርሻ ሥራው በተጨማሪ ሌሎች የገቢ ምንጮችን እንዲፈጥርና በዓመት ከአንድ ጊዜ በላይ እንዲያመርት እያስቻሉት ነው።


የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ዘላለም አለማየሁ እንዳሉት፤ የግብርና ልማት ሥራዎቹ በተቀናጀ መንገድ በመተግበራቸው አርሶ አደሩ የተሻሻሉ የእርሻ አሠራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምርቱን እያሳደገ ይገኛል።

በተለይም የኩታ ገጠም እርሻና የግብርና ሜካናይዜሽን ሥራዎችን በዘመናዊና በተቀናጀ መንገድ ለማከናወን እያገዙ መሆኑን ገልጸዋል።

በዞኑ በዘንድሮው የመኸር ወቅት ከ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች የለማ ሲሆን፣ ከዚህም ከ96 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል ነው ያሉት።

በዞኑ ከ80 በመቶ በላይ የግብርና ሥራ በሜካናይዜሽን እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህም የግብርናው ዘርፍ ወደ ዘመናዊ አሠራር እየተሸጋገረ መሆኑን አመላካች ነው ብለዋል።

የሜካናይዜሽን አጠቃቀም መስፋፋት አርሶ አደሩ ከምርቱ በሚያገኘው ገቢ ትራክተርና ኮምባይነር እስከ መግዛት እንዳስቻለውም አቶ ዘላለም ገልጸዋል።

በዞኑ ከመኸር እርሻ በተጨማሪ ከ600 ሺህ ሄክታር በላይ ተጨማሪ መሬትን በመስኖ ለማልማት እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በተለይም በመስኖ የሚከናወኑ የግብርና ሥራዎች ከቤተሰብ ፍጆታ በላይ ምርት እንዲገኝ፣ የአካባቢው ገበያ እንዲረጋጋና አርሶ አደሩ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝ እያገዙ መሆኑን አስረድተዋል።


የሲናና ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደበሌ ሀቤቤ በበኩላቸው፣ በወረዳው የስንዴ፣ የአትክልትና የማር ምርትን በኩታ ገጠምና በተቀናጀ አሠራር ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

በዘንድሮው የመኸር ወቅት በወረዳው ከ89 ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች የለማ ሲሆን ከልማቱም ከ20 በመቶ የሚበልጠው በመስኖ እየለማ መሆኑን ተናግረዋል።

ከልማቱም ከአንድ ሄክታር ከ40 እስከ 50 ኩንታል ምርት በአማካይ በማምረት በአጠቃላይ 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም በአርሶ አደር ማሠልጠኛ ማዕከላት የሚተገበሩ የተሻሻሉ የግብርና አሠራሮችን ወደ አርሶ አደሩ በማስፋፋት አበረታች ውጤት እየተገኘ መሆኑን ጠቁመዋል።


የሲናና ወረዳ አርሶ አደር አሸብር ከተማ በበኩላቸው፣ በአካባቢያቸው ጥቅል ጎመንና ካሮት በማምረት በአንድ የምርት ወቅት እስከ 500 ሺህ ብር ተጨማሪ ገቢ ማግኘት እንደቻሉ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም በአራት ሄክታር መሬት ላይ ተመሳሳይ ልማት እያካሄዱ ሲሆን፤ ከግብርና ሥራቸው በሚያገኙት ገቢም በሮቤ ከተማ ባለ ሁለት ወለል ዘመናዊ ሕንፃ እየገነቡና ልጆቻቸውንም በተሻለ ሁኔታ እያስተማሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ሌላው የወረዳው አርሶ አደር ሐጅ ፈይሰል ሐጅ አብዱረህማን በበኩላቸው፣ ከመደበኛ የስንዴ ልማታቸው በተጨማሪ በዓመት ሁለት ጊዜ የማር ምርት ለገበያ በማቅረብ እስከ 200 ሺህ ብር ተጨማሪ ገቢ እያገኙ መሆኑን አስረድተዋል።


ከግል ልማታቸው በተጨማሪ ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር በማኅበር በመደራጀት የማር ምርታቸውን እያሳደጉና እሴት በመጨመር ለገበያ እያቀረቡ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በአጠቃላይ በደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን እየተተገበሩ ያሉ የግብርና ልማት ኢኒሼቲቮች ምርትን ከማሳደግ ባለፈ የአርሶ አደሩን ገቢ በማሳደግ፣ ወደ ዘመናዊ ግብርና እንዲሸጋገርና ለገበያ የሚቀርብ ትርፍ ምርት እንዲያመርት እያገዙ መሆኑን መረጃዎቹ ያመለክታሉ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሐረር ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ከውበት ባለፈ የዜጎችን ኑሮና የንግድ እንቅስቃሴ በቀጥታ የሚያነቃቁ ናቸው

ሐረር፣ህዳር 15 /2019 ዓ.ም (ኢዜአ)፦ በሐረር ከተማ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ከውበት ባለፈ የዜጎችን ኑሮና የንግድ እንቅስቃሴ በቀጥታ የሚያነቃቁ...

Nov 25, 2026

ባለሀብቶች የግብርና ምርቶችን እሴት ጨምረው ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚነታቸውን እያሳደጉ ነው  

ሀዋሳ፣ ሕዳር1/2019(ኢዜአ)፡-የግብርና ምርቶችን እሴት ጨምረው ለውጭ ገበያ በማቅረብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እያሳደጉ መምጣታቸውን በግብርናው ዘርፍ የተሰ...

Nov 11, 2026

በክልሉ የገበያ ማዕከላትን ለማስፋፋትና ደረጃቸውን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷል

ሚዛን አማን፣ ጥቅምት 24/2019 (ኢዜአ)፡-በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቅዳሜና እሑድ ገበያ የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል የግብይት ማዕከ...

Nov 4, 2026

የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በፍጥነት ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው- የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ)፦የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር )በሌሎች አካባቢዎች የታየው ፈጣንና ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ በመቐለ ...

Nov 3, 2026