የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በምስራቅ ጎጃም ዞን በመኸር እርሻ እስካሁን ከ385 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል

Jul 30, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደብረ ማርቆስ ፤ሃምሌ 22/2018(ኢዜአ)፡- በምስራቅ ጎጃም ዞን በመኽር ወቅቱ እስከሁን ከ385 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ስብሎች ዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

በመምሪያው የሰብል ልማት ቡድን መሪ አቶ እምቢአለ አለኽኝ ለኢዜአ እንደገለጹት በያዝነው የመኸር ወቅት ከእለት ፍጆታ ባለፈ ለገበያ የሚተርፍ ምርት ለማምረት በትኩረት እየተሰራ ነው።

በምርት ወቅቱ ከ669 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች በማልማት 26 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል።

እስካሁን በተደረገ ጥረት ከ385 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል ።

በቆሎ፣ ገብስ፣ ስንዴ፣ ባቄላ፣ በሎቄ፣ ማሽላ፣ የቢራ ገብስ፣ ጤፍና ሌሎች ገበያ ተኮር ሰብሎች መዘራታቸውን ጠቅሰዋል።

በዘር ከተሸፈነው መሬት ውስጥም ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነውን በመስመር እንዲሁም ከ229 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነው ደግሞ በኩታገጠም የተዘራ መሆኑን አብራርተዋል።

ምርታማነትን ለማሳደግ በተደረገ ጥረትም ከ660 ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ጥቅም ላይ መዋሉን ተናግረዋል።


የመኸር እርሻው ከ390 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን በማሳተፍ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።

በዞኑ የጎዛምን ወረዳ የሸበልማ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር አንሙት የሻንበል እንደገለጹት የክረምቱን ዝናብ በመጠቀም ከአንድ ሄክታር በላይ መሬታቸውን በበቆሎና በስንዴ ሰብል መሸፈናቸውን ገልጸዋል።

ምርታማነታቸውን ለማሳደግም የግብርና ባለሙያን ምክረ ሃሳብ በመከተል ማዳበሪያ በመጠቀም፣ በኩታ ገጠምና በመስመር መዝራታቸውን አስረድተዋል።

የቀበሌው ነዋሪ አርሶአደር ይበልጣል ካሴ በበኩላቸው ባቄላ፣ ገብስና በቆሎ ሰብሎችን ቀድመው መዝራታቸውን ጠቁመው ጤፍ ለመዝራት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026

ባለፉት አምስት ዓመታት አዲስ አበባን የሰላምና የልማት ማዕከል ማድረግ ተችሏል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦ ባለፉት አምስት ዓመታት ስር የሰደዱ ችግሮችን በመቅረፍ አዲስ አበባን የሰላምና የልማት ማዕከል ማድረግ መቻሉን የአዲስ...

Jul 18, 2026

በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በሁሉም ዘርፍ ለትውልድ የሚሻገር የላቀ ዕድገት እያስመዘገበ ነው

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 16/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በሁሉም ዘርፍ ለትውልድ የሚሻገር የላቀ ዕድገት እያስመዘገ...

Jun 24, 2026