የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በክልሉ በመኸር እርሻ እስካሁን 1 ሚሊዮን 632 ሺህ ሄክታር ማሳ በተለያዩ የሰብል አይነቶች ለምቷል

Aug 27, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አሶሳ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመኸር እርሻ እስካሁን 1 ሚሊዮን 632 ሺህ ሄክታር ማሳ በተለያዩ የሰብል አይነቶች መልማቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

በተለይም እስካሁን ከለማው መሬት 231 ሺህ 902 ሄክታሩ በቅባት እህሎች የተሸፈነ መሆኑ ተመላክቷል።

በክልሉ ግብርና ቢሮ የሰብል ልማትና ጥበቃ ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ዳይሬክተር ፍቅሩ አቡን ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በክልሉ በመኸር ወቅቱ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር መሬት በተለያዩ የሰብል አይነቶች ለማልማት ታቅዶ ተግባራዊ እየተደረገ ነው።

እስካአሁን በተካሄደ የእርሻ ስራ 1 ሚሊየን 632 ሺህ ሄክታር ማሳ በተለያዩ የሰብል አይነቶች መልማቱን ተናግረዋል።

ከለማው ማሳ ውስጥም 231 ሺህ 902 ሄክታሩ በሰሊጥ፣ አኩሪ አተር እንዲሁም ለውዝ በመሳሰሉ የቅባት እህሎች የተሸፈነ መሆኑን ለአብነት ጠቅሰዋል።

አርሶ አደሮች በክልሉ ከሚገኘው የዘይት ፋብሪካ ጋር የገበያ ትስስር በመፈጠሩ የቅባት እህሎችን በስፋት በማምረት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በክልሉ የቅባት እህሎችን ምርታማነትን ለማሳደግ የተሻሻሉ ዝርያዎችን በመጠቀም እንዲሁም ለአርሶ አደሩ ተገቢውን ግንዛቤ በመፍጠር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በክልሉ ለቅባት እህሎች ተስማሚ የሚሆነውን የአካባቢ ስነምህዳር የመለየት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከአርሶ አደሩ በተጨማሪ በእርሻ ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሃብቶች በሰፋፊ የእርሻ ማሳ ላይ የቅባት እህሎችን በማምረት ለገበያ እያቀረቡ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026

ባለፉት አምስት ዓመታት አዲስ አበባን የሰላምና የልማት ማዕከል ማድረግ ተችሏል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦ ባለፉት አምስት ዓመታት ስር የሰደዱ ችግሮችን በመቅረፍ አዲስ አበባን የሰላምና የልማት ማዕከል ማድረግ መቻሉን የአዲስ...

Jul 18, 2026