የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የኢትዮጵያን የልማት ጉዞ ለማደናቀፍ የሚሞከሩ ውጫዊ ጫናዎች የሕዝቡን አንድነት ይበልጥ ያጠናክራሉ

Nov 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29/2019 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያን በውሃ ሀብቶቿን የማልማት ተግባር ለማደናቀፍ የሚሞከሩ ውጫዊ ጫናዎችና የተዛቡ ትርክቶች የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነት የሚሸረሽሩ ሳይሆን ይበልጥ አጠናክሮ በጋራ እንዲቆም የሚያደርጉ መሆናቸውን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ።

ኢትዮጵያ የምታካሂደው የልማት ሥራ ለቀጣናው ሀገራት ጭምር ጠቃሚ እንጂ ማንም ላይ የሚደርስ ጉዳት እንደሌለውም አመልክተዋል።

ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያን የውሃ ሀብት አጠቃቀምን በተመለከተ ከታሪክ አኳያ የሚነሱ የተሳሳቱ መረጃዎችና ትርክቶች እውነታውን የማያሳዩ ናቸው።

በኢትዮጵያ ወንዞችና የውኃ ሀብት ልማት ላይ የሚደረጉ የተሳሳቱ ስሌቶችና ስጋቶች ተገቢ እንዳልሆኑ ጠቁመዋል።


የኢትዮጵያ ዓላማ ሁልጊዜም የጋራ ጥቅምን ማዕከል ያደረገ እንጂ ሌሎችን የሚጎዳ እንዳልሆነ አስታውቀዋል።

ይሁን እንጂ የውጭ አካላት ኢትዮጵያ ውኃውን መጠቀም ከጀመረች እኛ እንጎዳለን ከሚል የተሳሳተ ስሌት በመነሳት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት እንዳይሳካ የተለያዩ መሰናክሎችን ሲፈጥሩ እንደቆዩ አስታውሰዋል።

ሆኖም በችግር ውስጥ አልፈውም የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት በጋራ በመቆም ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በርካታ የልማት ሥራዎችን እውን ማድረግ መቻላቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቶቿን ለማልማት የምታደርጋቸውን ጥረቶች ለማስተጓጎል የሚደረጉ ውጫዊ ግፊቶችና የተሳሳቱ የሚዲያ ዘመቻዎች የኢትዮጵያውያንን የአንድነት መንፈስ የሚፈትኑ ሳይሆን፣ ይበልጥ አጠናክረው በጋራ እንዲቆሙ የሚያደርጉ መሆናቸውንም አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ የውኃ ሀብቷን በፍትሃዊነትና በዘላቂነት ለሕዝቧ ልማት ለመጠቀም የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥልም ሚኒስትሩ አፅንኦት ሰጥቷል።


ኢትዮጵያ በታላቁ የሕዳሴ ግድብና በተለያዩ የልማት መስኮች እያከናወነቻቸው ያሉ የልማት ሥራዎች ግብፅን ጨምሮ ለቀጣናው ሀገራት ጠቃሚ እንጂ ሥጋት እንዳልሆኑ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅት የምንሰራው የልማት ሥራ ለኢትዮጵያም ለግብፅም ጭምር የሚጠቅም በመሆኑ ምንም ዓይነት ሥጋት ሊገባቸው አይገባም ሲሉ አስታውቀዋል።

የሀገራችንን የልማት እንቅስቃሴዎች ለማደናቀፍ የሚደረጉ ውይይቶች እና ፕሮፓጋንዳዎች ቢኖሩም፣ የኢትዮጵያ ትኩረት ሁልጊዜም በጋራ ልማት እና በውጤት ላይ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያን ከውጭ የሚሰነዘሩ ማናቸውንም ተንኮሎችና ሴራዎች በጋራ በመቆም ማሸነፍ የምንችል ጽኑ ሕዝቦች ነን ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም፣ ሀገራችን የምታከናውናቸውን የልማት ስራዎች እውነታና ትክክለኛ አቋም ለዓለም ማህበረሰብ በተለያዩ ቋንቋዎች ለማድረስ የሚደረጉ ጥረቶችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የአፍሪካ የልማት ተምሳሌቷ፡ዘላቂ መሠረተ ልማት እመርታ

አዲስ አበባ በለውጥ ጉዞዋ ውስጥ የጀመረችውን የከተማ ልማት እንቅስቃሴ ግለት ሳታስቀይር፣ የዘላቂ መሠረተ ልማት ግንባታዋን በማፋጠን ወደ ተቀናጀና ዘመናዊ ከተማ...

Nov 9, 2026

ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች ናቸው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች መሆና...

Oct 29, 2026

ሀብትን አውቆና አበልጽጎ ለትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር የመደመር መንግሥት ዋነኛ ዓላማ ነው - አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...

Oct 16, 2026

ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን የምታደርገው ጥረት ለቀጣናው ሰላም ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው

ዲላ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤት ለመሆን እያደረገች ያለው ጥረት ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ያላትን ቁ...

Oct 10, 2026