የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

12ኛው የአፍሪካ ምርት አቅርቦትና ፋሽን ሳምንት (ASFW Addis 2026) በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

Nov 13, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ህዳር 3/2019(ኢዜአ)፦12ኛው የአፍሪካ ምርት አቅርቦትና ፋሽን ሳምንት (ASFW Addis 2026) በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

የአፍሪካ ትልቁ የጨርቃጨርቅና የቆዳ ውጤቶች ኤግዚቢሽንም በአዲስ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በይፋ ተከፍቷል።

በማስጀመሪያ መርሀግብሩ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ዳጋቶ ኩምቤ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍጹም ከተማ እንዲሁም የበርካታ ሀገራት የዘርፉ ተዋንያን ተገኝተዋል።

‎በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የተገኙት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ዳጋቶ ኩምቤ ኢትዮጵያ ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ ከፍተኛ ተጨማሪ እሴት ያላቸው የቆዳና የጨርቃጨርቅ ምርቶች አምራችነት እየተሸጋገረች ነው ብለዋል።

መርሃ ግብሩ የኢንዱስትሪዎችን አቅም ለማሳየት፣ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለማስተዋወቅ፣ የንግድ ትብብሮችን ለማጠናከር፣ ልምድ ለመለዋወጥና የኢትዮጵያን ኢንዱስትሪዎች ከዓለም-አቀፍ ገበያዎች ጋር ለማገናኘት ዕድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

‎የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍጹም ከተማ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ለማጠናከር በርካታ ተግባራትን ማከናወኗን ገልጸዋል።

‎የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን (IPDC) በመላ አገሪቱ የሚገኙ 14 ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን እያስተዳደረ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

‎ኤግዚቢሽኑ ከዛሬ ጀምሮ አስከ ህዳር 6 ቀን 2019 ድረስ እንደሚቆይ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ ነው -ምሁራን

ጎንደር ፤ህዳር 2/2019 (ኢዜአ) ፡-የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን የዩኒቨ...

Nov 12, 2026

የአፍሪካ የልማት ተምሳሌቷ፡ዘላቂ መሠረተ ልማት እመርታ

አዲስ አበባ በለውጥ ጉዞዋ ውስጥ የጀመረችውን የከተማ ልማት እንቅስቃሴ ግለት ሳታስቀይር፣ የዘላቂ መሠረተ ልማት ግንባታዋን በማፋጠን ወደ ተቀናጀና ዘመናዊ ከተማ...

Nov 9, 2026

ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች ናቸው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች መሆና...

Oct 29, 2026

ሀብትን አውቆና አበልጽጎ ለትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር የመደመር መንግሥት ዋነኛ ዓላማ ነው - አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...

Oct 16, 2026