🔇Unmute
ዲላ፣ ህዳር 3/2019 (ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ የኃይል አማራጮችን ማስፋፋቷ የብዝሃ ኢኮኖሚ ውጤታማነትን ለማጠናከር ድርሻው የጎላ መሆኑን ምሁራን ገለጹ።
በዲላ ዩኒቨርሲቲ "የታዳሽ ኃይል ጥናትና ትምህርት በኢትዮጵያ" በሚል ርዕሰ አውደ ጥናት ተካሂዷል።
በአውደ ጥናቱም ከ22 በላይ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ዲን ተሻለ ወልደአማኑኤል (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት ኢትዮጵያ ከእጽዋት ተረፈ ምርት እስከ ኒውክሌር የብዝሃ ታዳሽ ኃይል ምንጭ የሚሆን ምቹ ሀብት ባለቤት ናት።
ሀገሪቱ ባለፉት ዓመታት ያከናወነቻቸው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች የታዳሽ ሃይል አቅሟን ያሳደገ እንዲሁም የአረንጓዴ ልማት ስራው ግድቦች በቂ ውሃ እንዲይዙ በማድረግ ለዘላቂ የኃይል አቅርቦት መኖር አቅም የፈጠረ ነው ብለዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ የልማት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ጭምር ነው ያሉት ምሁሩ ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል አጠቃቀምን ጨምሮ በአረንጓዴ ልማት ዓለም አቀፍ እውቅና ማግኘቷን ጠቅሰዋል።
ከውሃ፣ ከንፋስ፣ ከፀሐይ፣ ከጂኦተርማልና ከባዮጋዝ በተጨማሪ የሃይል ዘርፏን ወደ ኒውክሌር ጭምር ማስፏቷ የጀመረችውን ብዝሃ ኢኮኖሚ ውጤታማነት የሚያጠናከር ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የብዝሃ ታዳሽ ኃይል መገኛ ምንጭ ነች ያሉት ደግሞ በኖርወይ ላይፍ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሳሙኤል አዳራማላ ናቸው።
ይህንን ሃብት በቅንጅትና በትብብር ማልማት ከተቻለ ከምስራቅ አፍሪካ ቀጠና አልፎ የአፍሪካን የነዳጅ ጥገኝነት ጫናን የሚያቃልል ነው ብለዋል።
በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ውሃን ጨምሮ የታዳሽ ኃይልን በጋራ የመጠቀም አቋሟ የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህንን በጋራ አቀናጀተን መጠቀም ከቻልን በቀጠናው የነዳጅ ጥገኝነትን የሚያቃልል ነው። የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር) በበኩላቸው ኢትዮጵያ ኑውክሌርን ጨምሮ የኃይል አማራጯን ማስፋቷ የብዝሃ ኢኮኖሚ ትግብራ ውጤታማነትን ያጠናክራል ብለዋል።

በተለይ የኢትዮጵያ የኃይል ምንጯ ታዳሽ መሆኑ የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ለአካባቢ ጥበቃ መሰረት መጣሉን ጠቅሰው፣ ይህም ዓለም አቀፍ እውቅና በማግኝት የኮፕ-32 ጉባኤን እንድታዘጋጅ ለመመረጧ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው በቤተሰብ ደረጃ የባዮ ጋዝ ተጠቃሚነትንና በዘርፉ የማህበረሰቡን ግንዛቤን በማሳደግ የአካባቢውን የጥምር ደን ልማት እንዲስፋፋ ውጤታማ ተግባራት ማከናወኑን ተናግረዋል።
በአውደ ጥናቱ የሀገር ውስጥና የውጭ ተመራማሪዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ጎንደር ፤ህዳር 2/2019 (ኢዜአ) ፡-የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን የዩኒቨ...
Nov 12, 2026
አዲስ አበባ በለውጥ ጉዞዋ ውስጥ የጀመረችውን የከተማ ልማት እንቅስቃሴ ግለት ሳታስቀይር፣ የዘላቂ መሠረተ ልማት ግንባታዋን በማፋጠን ወደ ተቀናጀና ዘመናዊ ከተማ...
Nov 9, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች መሆና...
Oct 29, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...
Oct 16, 2026