🔇Unmute
ጎባ ፤ ህዳር 03/2019(ኢዜአ)፦ በደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን የእንስሳት ዝርያን በማሻሻል ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ በተሰሩ ሥራዎች ውጤት እየታየ መምጣቱን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ።
በዞኑ በሰው ሰራሽ ስነ-ዘዴ የወተት ላሞች ማዳቀልና የዝርያ ማሻሻያ ስራ የዞኑ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ በጎባ ወረዳ ተካሂዷል።

የደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ዘላለም አለማየሁ በወቅቱ እንዳሉት በዞኑ ባለፉት ዓመታት የእንስሳት ዝርያን በማሻሻል ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት እየታየ ነው።
በተለይም ባለፉት ዓመታት የወተት ላሞችን በሰው ሰራሽና በመደበኛ መንገድ በማዳቀል የእንስሳት ሀብት ልማቱን ለማሳደግ ውጤታማ ስራ ተከናውኗል ብለዋል።
በዞኑ ባለፉት ዓመታት በስፋት የማይታወቀው በሰው ሰራሽ ስነ ዘዴ የተሻሻሉ የእንስሳት ዝርያዎች የማዳቀሉ ተግባር አሁን ላይ በስፋት እየተተገበረ መምጣቱን አስታውሰዋል።

በዚህም ከአካባቢው ዝርያ ላሞች በቀን ይገኝ የነበረውን ሁለት ሊትር የማይበልጠውን ወተት ከ12 እስከ 20 ሊትር ማሳደግ የተቻለ ሲሆን፤ የዞኑን ዓመታዊ የወተት ምርትና ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ማሳደግ እንደተቻለም አብራርተዋል።
አቶ ዘላለም እንዳሉት በተያዘው የበጀት ዓመትም በዞኑ 63 ወረዳዎች ውስጥ ከ900 ሺህ በላይ ላሞችን ለማዳቀል ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን አረጋግጠዋል።
እስከ አሁን በተከናወነው የሥራ እንቅስቃሴም 45 በመቶ የሚሆነውን ማከናወን መቻሉንና ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን አክለዋል።
በጎባ ወረዳ የእንስሳት ዝርያ በማሻሻል የሚገኘውን ውጤት ማሳደግ ዓላማ ያደረገው ሥራ የዚሁ ጥረት አካል እንደሆነም አቶ ዘላለም አመልክተዋል።
በወረዳው የወተት ላሞችን በሰው ሰራሽና በመደበኛ መንገድ በማዳቀል የእንስሳት ሀብት ልማቱን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የጎባ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አበባ ጌታቸው ናቸው።
በወረዳው በበጀት ዓመቱ ለማሳካት ከተያዘው 20 ሺህ የወተት ላሞች በሰው ሰራሽ ስነ ዘዴና በመደበኛ መንገድ የማዳቀል ሥራ ውስጥ 40 በመቶ ማከናወን መቻሉን አስታውቀዋል።
አርሶ አደሩም የእንስሳት ዝርያውን በማሻሻል ከዘርፉ የሚገኛው ውጤት ለማሳደግ ሙያዊ ድጋፍና ክትትል እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።
በዚህም ከዘርፉ የሚገኛው ውጤትና የተጠቃሚው ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን አስተውሰዋል።
አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ የጎባ ወረዳ አርሶ አደሮች መካከል አቶ ግዛቸው ተሾመ ከዚህ ቀደም ካላቸው የአካባቢ ላሞች የሚያገኙት ሁለት ሊትር ወተት እንደነበር በማስታወስ አሁን ላይ ዝርያቸው ከተሻሻሉ ላሞች በቀን ከአንዲት ላም ወደ 15 ሊትር እንደሆነ ገልጸዋል።
ላሞችን በሰው ሰራሽ ስነ-ዘዴ ማዳቀል ከጀመሩ ወዲህ ከአንድ ላም በቀን 20 ሊትር ወተት ማግኘት መጀመራቸውና ቴክኖሎጂውን እያስፋፉ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ ሌላው የወረዳው ነዋሪ ወይዘሮ ገነት ከበደ ናቸው።
ጎንደር ፤ህዳር 2/2019 (ኢዜአ) ፡-የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን የዩኒቨ...
Nov 12, 2026
አዲስ አበባ በለውጥ ጉዞዋ ውስጥ የጀመረችውን የከተማ ልማት እንቅስቃሴ ግለት ሳታስቀይር፣ የዘላቂ መሠረተ ልማት ግንባታዋን በማፋጠን ወደ ተቀናጀና ዘመናዊ ከተማ...
Nov 9, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች መሆና...
Oct 29, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...
Oct 16, 2026