🔇Unmute
አዲስ አበባ፣ ህዳር 6/2019 (ኢዜአ)፦ የመደመር መንግሥት የፓፓና ሙዝ ፍራፍሬ ልማት ኢኒሼቲቭ የሥራ ባህል በመቀየር ወደ ትርፍ አምራችነት እንዳሸጋገራቸው በማዕከላዊ ኦሮሚያ ዞን የቦራ ወረዳ ወጣቶች ገለጹ።
ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ራዕይ
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጋር በመተባበር በጅማ ከተማ የሚከበረውን 21ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በማስመልከት የመገናኛ ብዙሃን የመስክ ጉብኝት እያካሄደ ነው።
በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ጸጋዎችን ለማስተዋወቅ በተዘጋጀው ጉብኝት በመደመር እሳቤ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን መመልከት ተችሏል።

በማዕከላዊ ኦሮሚያ ዞን ቦራ ወረዳ በፓፓያ ልማት ላይ የተሰማራው ወጣት ፋሲካ ተስፋዬ ሥራውን የጀመረው ከሁለት ዓመት በፊት እንደነበር ይገልጻል።
በወቅቱ የግብርና ባለሙያዎች ፓፓያ እንዲያለማ ሲያማክሩት ፈቃደኛ እንዳልነበረ ገልጾ፤ ከብዙ ምክክር በኋላ በነፃ የቀረበ ስለሆነ ለሙከራ በሚል መትከሉን ያስታውሳል።
ይሁን እንጂ ፓፓያው በሚደንቅ ፍጥነትና ጥራት ምርት መስጠት መጀመሩ የመንግሥትን ኢኒሼቲቭ ትክክለኛነት ማረጋገጡን ተናግሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ቦራ ወረዳ ሲመጡ መጀመሪያ የጎበኙት የእሱን የፓፓያ ማሳ እንደነበርም በማስታወስ አካባቢው በፓፓያና ሙዝ ክላስተር ምርት የሚታወቅ ሆኗል ብሏል።
ይህ መሬት ከዓመታት በፊት በዓመት አንዴ የምንጎበኘው ነበር የሚለው ወጣት ፋሲካ፣ አሁን ላይ ሙሉ ቀን የማይለዩት አረንጓዴ፣ ነፋሻማና የምርት ሥፍራ መሆኑን ገልጿል።
በዓመት ሁለት ጊዜ ምርት እንደሚሰጥና የመንግሥት ያላሰለሰ ጥረትና እርዳታ ለዚህ እንዳበቃቸው ጠቁሞ መንግሥት የአይቻልም እሳቤን ከውስጣችን እንድናስወጣ ማስቻሉን ተናግሯል።
በክላስተር ልማት ማሳቸውን በጋራ ለመንከባከብ፣ በሽታን በትብብር ለመከላከል፣ ሰፊ የገበያ ዕድል ለመፍጠርም የጎላ አበርክቶ እንዳለው አንስቷል።

በቦራ ወረዳ በሙዝ ክላስተር ልማት የተሰማራው ወጣት አብሹ ደምሴ፣ የአካባቢው ማኅበረሰብ መሬቱን ለኮንትራት አምራች እንጂ ራሱ የማልማት ልምድ አልነበረውም ብሏል።
በዚህም ማኅበረሰቡ በተለይ ወጣቶች በራሳቸው የእርሻ መሬት የበይ ተመልካች ሆነው መቆየታቸውንም ነው ያስታወሰው።
ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ መንግሥት ወጣቶችን በክላስተር በማደራጀት በሙዝ ምርት እንዲሳተፉ በማድረግ ነገ ተስፋ እንዲኖራቸው ማድረጉን ገልጿል።
በወረዳው 27 ወጣቶች በመደራጀት በ102 ሄክታር መሬት ላይ ሙዝ በክላስተር እያለሙ ራሳቸውን እየለወጡ እንደሚገኙ ጠቁሞ ለዚህም መንግሥት ምስጋና ይገባዋል ብሏል።
ሌላው በፓፓያ ክላስተር ልማት የተሰማራው ወጣት ሽመልስ መብራት በክላስተር ከሚለማው ፓፓያ ሦስት ጊዜ በመልቀም የተሻለ ገቢ ማግኘቱን ገልጿል።
መንግሥት በክላስተር እንድናለማ ዕድሉን ከማመቻቸት ባለፈ የግብርና ባለሙያዎች ምክርና የግብርና ግብዓት በቀላሉ እንድናገኝ አስችሎናል ብሏል።
የቦራ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ዳሉ ደደሮ በወረዳው ከ320 ሄክታር በላይ መሬት በፓፓያና ሙዝ ክላስተር እየለማ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የክላስተር ልማቱ የአርሶ አደሮችን የሥራ ባህል በመቀየር ወደ ትርፍ አምራችነት እንዲሸጋገሩ አስችሏቸዋል ሲሉም አረጋግጠዋል።
ቀደም ሲል አርሶ አደሩ በራሱ ማሳ አይጠቀምም ነበር ያሉት ምክትል አስተዳዳሪው፤ ምርቱን እንደ ቋሚ ንብረት በማስያዝ ብድር የሚያገኝበት ዕድል መፈጠሩንም ተናግረዋል።
ጎንደር ፤ህዳር 2/2019 (ኢዜአ) ፡-የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን የዩኒቨ...
Nov 12, 2026
አዲስ አበባ በለውጥ ጉዞዋ ውስጥ የጀመረችውን የከተማ ልማት እንቅስቃሴ ግለት ሳታስቀይር፣ የዘላቂ መሠረተ ልማት ግንባታዋን በማፋጠን ወደ ተቀናጀና ዘመናዊ ከተማ...
Nov 9, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች መሆና...
Oct 29, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...
Oct 16, 2026