የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በወላይታ ሶዶ ከተማ ከ12 ኪሎ ሜትር በላይ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ሥራ እየተከናወነ ነው

Nov 17, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ወላይታ ሶዶ፤ ሕዳር 7/2019 (ኢዜአ)፦ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከ12 ኪሎ ሜትር በላይ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ሥራን በውሉ መሰረት ለማጠናቀቅ በርብርብ እየተሰራ መሆኑን ተገለጸ።


ግንባታውን በማስመልከት ኢዜአ ያነጋገራቸው በፌዴራል መንገዶች አስተዳደር የሶዶ ፕሮጀክቶች አስተዳደር ጽህፈት ቤት የወላይታ ሶዶ አስፋልት ፕሮጀክት መሃንዲስ ኢንጂነር አክሊሉ አሳሌ እንደገለጹት፣ መንገዱ እየተገነባ ያለው በሁለት ሎት ተከፍሎ ነው።

የግንባታ ሥራው ከፌደራል መንግስት በተመደበ 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት መሆኑንም ተናግረዋል።

አንደኛው ሎት በከተማው ከሌዊ እስከ ግብርና ኮሌጅ የሚገነባው የ7 ነጥብ 14 ኪሎ ሜትር መንገድ ሲሆን ሁለተኛው ከካዎ ጦና አደባባይ እስከ አረካ መገንጠያ ድረስ የሚገነባው የ5 ነጥብ 25 ኪሎ ሜትር ነው።

በሁለቱም አቅጣጫ የሚገነቡ መንገዶች በድምሩ 12 ነጥብ 39 ኪሎ ሜትር መሆናቸውን ገልጸው፣ በአሁኑ ወቅት የመንገዶቹ ግንባታ አፈጻጸም ከ78 በመቶ በላይ መድረሱን ጠቁመዋል።

የመንገዶቹ ግንባታ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2023 ተጀምሮ 2025 ዓ.ም ለማጠናቀቅ ታቅዶ ቢጀምርም ከወሰን ማስከበር፣ ተጨማሪ የኮሪደር ልማት ሥራዎች መካተታቸውና መሰል ምክንያቶች ሥራው ተጓቶ እንደነበር የገለጹት ደግሞ የከተማው ማዘጋጃ ቤት ኃላፊ አቶ ፍሬው ሻንካ ናቸው።

የሥራ ተቋራጩ ከአሰሪው ተቋም ጋር በገባው የጊዜ ማራዘሚያ ተጨማሪ ውል ስምምነት መሰረት እስከ መጪው የካቲት ወር መጨረሻ ድረስ ለማጠናቀቅ ሌት ተቀን እየተሰራ ነው ብለዋል።

በተለይ የቀድሞውን ዋና መንገድ ይዞ የሚያልፈው የሎት አንድ ግንባታ መጓተቱ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ ቢቆይም በመደመር መንግስት በተቀመጣ አቅጣጫ መሰረት ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በፍጥነት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የከተማው ማዘጋጃ ቤት የማሽነሪዎች፣ የጭነት መኪኖች እና የነዳጅ እጥረት እንዳይከሰት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም አመልክተዋል።

የመንገድ ግንባታው ሥራ ተቋራጭ የቻይናው ፈርስት ሃይ ዌይ ኢንጂነርንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ሀን ባዮሚንግ በበኩላቸው፤ ከ600 በላይ ሠራተኞችን በማሰማራት ግንባታውን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የአስፋልት እና የቤዝ ኮርስ ሥራዎች በመፋጠን ላይ መሆናቸውን ገልጸው፣ መንገዱን በውሉ መሰረት ለማጠናቀቅ አስፈላጊ ማሽኖችን ቁጥር በማሳደግ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

"የመንገዱ ግንባታ መስተጓጎል በከተማዋ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሮ ነበር" ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡተ ደግሞ የከተማው ነዋሪ ሻለቃ ጳውሎስ ገብረስላሴ ናቸው።

ወይዘሮ የኔዓለም ሳሙኤል የተባሉ ነዋሪ በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት ግንባታው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመው፣ አሰራሩ በዚህ ከቀጠለ በፍጥነት ተጠናቆ ለአገልግሎት ይበቃል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ ነው -ምሁራን

ጎንደር ፤ህዳር 2/2019 (ኢዜአ) ፡-የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን የዩኒቨ...

Nov 12, 2026

የአፍሪካ የልማት ተምሳሌቷ፡ዘላቂ መሠረተ ልማት እመርታ

አዲስ አበባ በለውጥ ጉዞዋ ውስጥ የጀመረችውን የከተማ ልማት እንቅስቃሴ ግለት ሳታስቀይር፣ የዘላቂ መሠረተ ልማት ግንባታዋን በማፋጠን ወደ ተቀናጀና ዘመናዊ ከተማ...

Nov 9, 2026

ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች ናቸው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች መሆና...

Oct 29, 2026

ሀብትን አውቆና አበልጽጎ ለትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር የመደመር መንግሥት ዋነኛ ዓላማ ነው - አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...

Oct 16, 2026