የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በአዳማ ከተማ አስተዳደር አራት ወራት 9 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰበሰበ

Nov 18, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዳማ፤ ህዳር 8/2019 (ኢዜአ)፡- በአዳማ ከተማ አስተዳደር በበጀት ዓመቱ ባለፉት አራት ወራት 9 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የአስተዳደሩ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ገለጸ።

የከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ በላቸው አሰፋ ለኢዜ እንዳስታወቁት የከተማውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዕድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ዘመናዊ፣ ፍትሃዊ እና ቀልጣፋ የግብር አሰባሰብ ስርዓት ተዘርግቶ እየተሰራ ይገኛል።

የገቢ ተቋሙን የአገልግሎት አሰጣጥ ማዘመን፣ አሰራሩን በቴክኖሎጂ ማስደገፍ እና ያሉትን የገቢ አማራጮች አሟጦ የመጠቀም እንዲሁም የፈፃሚውን አቅም መገንባት ደግሞ ትኩረት ከተሰጣቸው ተግባራት ናቸው።

በከተማው በ2019 በጀት አመት ከተለያዩ የገቢ ምንጮች ከ32 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።

በዚህም ባለፉት አራት ወራት በተካሄደው የተቀናጀ እንቅስቃሴ ከቀጥታ ታክስ፣ ቀጥታ ካልሆነ ታክስና ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት 9 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ወራት የገቢ ግብር አፈፃፀም አበረታች መሆኑን ገልጸው፤ የታቀደውን ለማሳካት የከተማ አስተዳደሩ የግብር አሰባሰብ ግብረ ሃይልም ድጋፍና ክትትል እያደረገ ነው ብለዋል።


በከተማ አስተዳደሩ የተደረገው የገቢ አሰባሰብ ሪፎርም የተገልጋይን እርካታ ከማሳደግ ባለፈ፣ የከተማዋን ገቢ በብቃት ለመሰብሰብ ምቹ መደላድል ፈጥሯል ብለዋል።

ለከተማው ግብር ከፋዮች በተሰጠው ግንዛቤ መሠረት፣ ግብራቸውን በታማኝነትና በተነሳሽነት በወቅቱ እየከፈሉ እንደሚገኙም አብራርተዋል።

ህብረተሰቡ ለሚፈፅመው ግብይት ደረሰኝ በመቀበል ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ጠቁመው፤ ይህን የማይፈጽሙ ነጋዴዎችን በማጋለጥ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።

ከግብር ከፋዮች መካከል አቶ ጌዲዮን ማሪ በበኩላቸው በከተማዋ የአንድ ፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ መሆናቸውን ገልጸው፤ ግብር በወቅቱ በመክፈል የዜግነት ግዴታቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

ግብራችንን ባለንበት ሆነን በበይነመረብ ነው የምንከፍለው ያሉት አስተያየት ሰጪው፤ ይህም የግብር አሰባሰብ ስርዓቱ ይበልጥ ዘመናዊና ቀልጣፋ እንዲሆን እያስቻለ ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በየሦስት ወሩ ይከፈል የነበረው ግብር፣ ካለፈው ዓመት ወዲህ በየወሩ እንዲከፈል መደረጉ ያለ ውዝፍ በወቅቱ ለመፈጸም እንዳስቻላቸው ነው የተናገሩት።

አቶ ጌዴዮን ሁሉም ዜጋ ግብርን በወቅቱ በመክፈል የከተማዋን ብሎም የሀገርን የልማት ፍላጎት በማሟላት ረገድ የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አመልክተዋል።

በአዳማ ከተማ አስተዳደር በ2018 በጀት ዓመት ከ21 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ከጽህፈት ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ ነው -ምሁራን

ጎንደር ፤ህዳር 2/2019 (ኢዜአ) ፡-የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን የዩኒቨ...

Nov 12, 2026

የአፍሪካ የልማት ተምሳሌቷ፡ዘላቂ መሠረተ ልማት እመርታ

አዲስ አበባ በለውጥ ጉዞዋ ውስጥ የጀመረችውን የከተማ ልማት እንቅስቃሴ ግለት ሳታስቀይር፣ የዘላቂ መሠረተ ልማት ግንባታዋን በማፋጠን ወደ ተቀናጀና ዘመናዊ ከተማ...

Nov 9, 2026

ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች ናቸው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች መሆና...

Oct 29, 2026

ሀብትን አውቆና አበልጽጎ ለትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር የመደመር መንግሥት ዋነኛ ዓላማ ነው - አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...

Oct 16, 2026