የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍሰትን በማሳደግ ኢኮኖሚውን የሚያጎለብት ተግባራት እየተከናወኑ ነው

Nov 19, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሐረር፤ ህዳር 09/2019 (ኢዜአ)፦ የሐረሪ ክልልን ምጣኔ ሀብት ለማሳደግ የኢንቨስትመንት ፍሰትን የሚያጠናክሩ የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን የክልሉ ኢንተርፕራይዞች ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቀ።

በሐረሪ ክልል ምጣኔ ሀብቱን በዘላቂነት ለማሳደግ የአምራች ኢንዱስትሪውንና የኢንቨስትመንት ዘርፉን በስፋት የማነቃቃት ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የክልሉ መንግሥት የኢንቨስትመንት ፍሰቱን ለማሳደግ የአሠራር ሥርዓቶችን በማዘመን፣ የመሠረተ ልማት አቅርቦትን በማሻሻልና ፈጣን አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

በተለይም በአምራች ኢንዱስትሪ፣ በግብርና ማቀነባበሪያ፣ በአገልግሎትና በሆቴል ዘርፎች ለሚሰማሩ ባለሀብቶች የሚደረገው ድጋፍና ማበረታቻ የኢንቨስትመንት ፍላጎቱን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር አድርጎታል።

በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ብቻ ከ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 51 አልሚዎች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱም የዚሁ ጥረት አንዱ ማሳያ ነው።

እነዚህ ፕሮጀክቶች ወደ ሙሉ ትግበራ ሲገቡም በክልሉ ሰፊ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ፣ የምርትና አገልግሎት አቅርቦትን በማሳደግ የክልሉን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግሩታል ተብሎ ይታመናል።

የክልሉ ኢንተርፕራይዞች ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሰሚር አብዱላሂ እንዳገለጹት፤ ቢሮው የኢንቨስትመንት ፍሰትን በማሳደግ ኢኮኖሚውን የሚያጎለብትና የሥራ ዕድል ፈጠራን የሚያጠናክሩ ተግባራት እያከናወነ ነው።

በክልሉ ለኢንቨስትመንት ዘርፉ ውጤታማና ቀልጣፋ አሰራርን በመዘርጋት ለአዳዲስ አልሚዎች የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት በተደረገው ጥረት፤ በሩብ ዓመቱ ባጠቃላይ ለ51 አልሚዎች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን ገልጸዋል።

ፈቃዱ ከተሰጣቸው አልሚዎች 12ቱ በሆቴል፣ ዘጠኙ በማኑፋክቸሪንግ ሲሆኑ ቀሪዎቹ በግብርናና በሌሎች ዘርፍ ፈቃድ የተሰጣቸው መሆኑን ጠቁመው፤ ጠቅላላ የካፒታል መጠናቸውም ከ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ ገልጸዋል።

በክልሉ ከዚህ ቀደም ፈቃድ ወስደው የነበሩ ፕሮጀክቶች በሩብ ዓመቱ ወደ ማምረትና አገልግሎት መስጠት በመሸጋገር ለዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እንደፈጠሩም ጠቅሰዋል።

በክትትልና ቁጥጥር ተግባራት በ58 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ላይ የእርምት እርምጃዎች መወሰዳቸውን ጠቁመዋል።

በዚህም 15 ፕሮጀክቶች የቃል ማስጠንቀቂያ፣ 26 የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ፣ 10 ፕሮጀክቶች እገዳ የተጣለባቸው ሲሆን፤ የሰባት ባለሀብቶች ፕሮጀክቶች ደግሞ ፈቃዳቸው መሰረዙን አስታውቀዋል።

በክልሉ ለኢንቨስትመንት ዘርፉ የሚደረገው ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ምክትል ቢሮ ሃላፊው አክለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ ነው -ምሁራን

ጎንደር ፤ህዳር 2/2019 (ኢዜአ) ፡-የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን የዩኒቨ...

Nov 12, 2026

የአፍሪካ የልማት ተምሳሌቷ፡ዘላቂ መሠረተ ልማት እመርታ

አዲስ አበባ በለውጥ ጉዞዋ ውስጥ የጀመረችውን የከተማ ልማት እንቅስቃሴ ግለት ሳታስቀይር፣ የዘላቂ መሠረተ ልማት ግንባታዋን በማፋጠን ወደ ተቀናጀና ዘመናዊ ከተማ...

Nov 9, 2026

ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች ናቸው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች መሆና...

Oct 29, 2026

ሀብትን አውቆና አበልጽጎ ለትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር የመደመር መንግሥት ዋነኛ ዓላማ ነው - አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...

Oct 16, 2026