የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ የከብት እርባታ

Nov 19, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ የከብት እርባታ፤ የአምቦ እህትማማቾች አበረታች የስኬት ጉዞ

በትምህርት ዓለማቸው የኢንፎርሜሽን ሲስተም እና የሶፍትዌር ቴክኖሎጂ ምሩቃን ወጣት ኤኙማ ዴቢሳ እና ታደሱ ዴቢሳ፤ ማህበረሰቡ ለሴቶች ከሰጠው አመለካከት እና ከተቀጣሪነት አስተሳሰብ በመላቀቅ፣ የተማሩትን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ከባህላዊ የግብርና ዕውቀት ጋር አቀናጅተው በእንስሳት እርባታ ዘርፍ ታላቅ ስኬት እያስመዘገቡ ይገኛሉ።

ከአባታቸው ከአቶ ደቢሳ ነጋሳ በተቀበሉት የትጋት እሴት እና መንግስት ከፈጠረላቸው የፋይናንስና የቦታ ምቹ ሁኔታ ጋር በመቀናጀት፣ "ታደሱ ዴቢሳ እና ጓደኞቻቸው" በተሰኘ ድርጅታቸው አማካኝነት በአሁኑ ወቅት በአራተኛው ዙር የንግድ ስራቸው 30 የቦረና ከብቶችን በዘመናዊ መንገድ በማደለብ ላይ ናቸው።

የመደመር መንግሥት ለግብርናው ዘርፍ የሰጠውን ቀዳሚ ትኩረት ተከትሎ፣ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲዎችን መሠረት ያደረጉ ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ ይገኛሉ።

በተለይም ወጣቶች ከተቀጣሪነት አስተሳሰብ ወጥተው የራሳቸውን ሥራ እንዲፈጥሩ ለማስቻል ከሲንቄ ባንክ እና ከሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የብድር፣ የቦታ እና የግብር አሰራር ድጋፎች እየተደረጉ ናቸው።

ይህ የመንግሥት ዕንቅስቃሴ ወጣቶች በሀገራቸው ሀብት ላይ ተመስርተው በፈጠራና በሥራ ፈጣሪነት እንዲሰማሩ ትልቅ አቅም የፈጠረና የሁሉንዮሽ አድማስ የከፈተ በመሆኑ፣ የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባለፈ ለሀገራዊ ዕድገት የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

እህትማማቾቹ ኤኙማ ዴቢሳ እና ታደሱ ዴቢሳ በተማሩት የኢንፎርሜሽን ሲስተም እና የሶፍትዌር ቴክኖሎጂ ትምህርት በመታገዝ፣ የወደፊቱ የእንስሳት እርባታ በቴክኖሎጂ፣ በፈጠራ፣ በመረጃ እና በዘመናዊ አስተዳደር ላይ መመስረት እንዳለበት በተግባር እያሳዩ ነው።

ዓላማቸው ከብቶችን ማርባት ብቻ ሳይሆን፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የእንስሳትን ጤና፣ የምርት ጥራት፣ ምርታማነትና የእርሻ አስተዳደርን ማሻሻል ነው።

በዚህም መሠረት በወተት ላሞች እርባታና በስጋ ከብቶች ማደለብ ስራቸው ላይ ቴክኖሎጂን በስድስት ዋና ዋና መንገዶች በማካተት እየሰሩ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡

በዚህም ዲጂታል የእርሻ አስተዳደር፣ የእንስሳት መለያና ክትትል፣ ዘመናዊ የመኖ አስተዳደር፣ ዘመናዊ የወተት ምርት ቴክኖሎጂ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ዘላቂ ግብርናና የቆሻሻ መልሶ አጠቃቀም እየሰሩ መሆናቸውን ይጠቅሳሉ፡፡

በቴክኖሎጂ ዘርፍ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት ሁለቱ እህትማማቾች ኤኙማ እና ታደሱ፣ ከተቀጣሪነት ወጥተው በአባታቸው አርአያነት በቦረና ከብት እርባታ ላይ የተሰማሩበት ድንቅ ስኬት ለሌሎች ወጣቶች አዲስ ተስፋንና አርአያን እየፈጠረ ይገኛል።

የቤተሰባቸው የግብርና ዳራ እና የአባታቸው መመሪያ ለዚህ ሥራ መሠረት እንደሆናቸው ኢዜአ ባነጋገራቸው ወቅት ገልጸዋል።

ኤኙማ ዴቢሳ በኢንፎርሜሽን ሲስተም ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2013 ዓ.ም በመመረቅ በግራጁዌት አሲስታንትነት እና በሌክቸረርነት ማገልገሏን ገልጻ፣ በተለያዩ የግል ድርጅቶችም መሥራቷን ታስታውሳለች።

ታደሱ ዴቢሳ በበኩሏ በሶፍትዌር ኩባንያ ውስጥ በመስራት እና ወጣቶችን በማስተማር ስታገለግል እንደነበር ትገልጻለች።

"እኛ ሁለቱ እህትማማቾች ተቀጥረን ብቻ መሥራት ለቤተሰብም ሆነ ለሀገር ኢኮኖሚ ትልቅ ለውጥ እንደማያመጣ በማመን፣ የራሳችንን ሥራ ፈጥረን ለመሥራት ተነሳስተናል" የምትለው ኤኙማ፤ ሥራውን ሲጀምሩ በመጀመሪያ የወተት ላሞችን ይዘው የነበረ ቢሆንም፣ ቆይተው ወደ ከብት ማደለብ ዘርፍ መግባታቸውን ታስረዳለች።

ወደ ከብት ማደለብ ሥራ ሲገቡም መጀመሪያ በያቤሎ በኬ ገበያ 10 ከብቶችን በመግዛት ወደ ሥራ መግባታቸውን ጠቅሳ፣ የቦረና ከብቶች ሥጋ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተፈላጊነት ስላለው ጥራት ያለው ሥጋ ለሀገር ውስጥ ገበያ ማቅረብ መፈለጋቸውን ተናግራለች።

በተጨማሪም የቦረና ከብቶች ዝርያ እንዳይጠፋ በደንብ በማራባት ጥሩ የጄኔቲክ ማሻሻያ ሥራ መሥራት እንደሚፈልጉም ገልጻለች።

አሁን ላይ ሥራቸው እያደገ መጥቶ ወደ አራተኛው ዙር መሸጋገራቸውን የገለጸችው ኤኙማ፤ ሙሉ ቤቱ ሞልቶ 30 የቦረና ከብቶችን በማደለብ ላይ እንደሚገኙ ጠቅሳለች።

" ከዚህ ቀደም የተሸጡት ሁለት ዙር ከብቶች ለደንበኞቻችን ከፍተኛ እርካታ የሰጡ ሲሆን፣ ደንበኞችም በስጋው ጥራት ተደስተው አበረታች ግብረ-መልስ ሰጥተውናል። በዚህም የራሳችንን ስኬት ገንብተናል" ብላለች።

መማር ማለት ዲግሪ ይዞ መቀመጥ ሳይሆን፣ ነገሮችን በተለያየ እይታ በመመልከትና ወጪን አስቀድሞ በሂሳብ ስሌት በመለካት ስራን በብቃት መምራት መሆኑን ትገልጻለች።

"አሁን ላይ ሥራችን በገንዘብ ማግኛ ብቻ ሳይሆን በግል ራዕይ የሚመራ ነው" ስትል የገለጸችው ታደሱ ዴቢሳ፣ በየቀኑ ጠዋት ማለዳ በ11 ሰዓት ወደ ሥራ ቦታዋ ስትመጣ ትልቅ አላማን ሰንቃ እንደምትንቀሳቀስ ትናገራለች።

ቴክኖሎጂ ከግብርና የተለየ ነገር ሳይሆን የዘመናዊ እርባታ ዋና አካል እንደሆነ የሚያምኑት እህትማማቾቹ፣ የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊ የእንስሳት ሀብት፣ በተለይም የቦረና ከብትን፣ ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ፣ ከጥራት ያለው አመጋገብና ከጥሩ አስተዳደር ጋር በማቀናጀት የሀገሪቱን የእንስሳት እርባታ ወደ ከፍተኛ ደረጃ የማሸጋገር ራዕይ እንዳላቸው ትናገራለች።

በዘርፉ ትልቅ የግብርና ኩባንያና ዘመናዊ የከብት እርባታ ጣቢያ (ራንች) በመክፈት የገጠር ወጣቶችን ማስተማርና ማሰልጠንም ቀጣይ ግባቸው መሆኑንም እንዲሁ፡፡

"ልጆቼን እያየሁ በጣም ደስ ብሎኛል" የሚሉት አባትየው አቶ ደቢሳ ነጋሳ በበኩላቸው፣ የተማረ ልጅ ከወላጆቹ ጋር መሥራቱን እንደ ኋላቀርነት ማየት መቋረጥ እንዳለበት ይናገራሉ።

ወላጆች የልጆቻቸውን ራዕይ እንዲደግፉና "ሰው ምን ይለኛል?" ከሚል አባባል በመውጣት በሥራ ላይ እንዲያተኩሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በመንግስት በኩል ከሲንቄ ባንክ እና ከሌሎች ተቋማት ጋር በመተባበር የተመቻቸውን የብድርና የቦታ ዕድል በአግባቡ በመጠቀም ወጣቶች ራሳቸውን መለወጥ እንደሚችሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጣቶች የዕለት ተዕለት የህይወት ግባቸውንና የወደፊት ዕቅዳቸውን ለማሳካት፣ በቤተሰባቸው መሬት እና በራሳቸው አቅም ላይ በመመስረት ዝቅ ብሎ የመሥራት ባህልን ማዳበር እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ወላጆች ልጆቻቸው ከፍተኛ ትምህርታቸውን አጠናቀው ሲወጡ "ከእኛ ጋር በግብርና ስራ ላይ ይሰማራሉ?" በሚል ከማማረር ወጥተው፣ የልጆቻቸውን ፈጠራና ራዕይ በመደገፍ እንዲሁም ያላቸውን አቅም አስተባብረው ለላቀ ድል ማብቃት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በአጠቃላይ በመንግስት በኩል የተመቻቹትን የቦታ አቅርቦቶች እና የፋይናንስ ብድር ዕድሎች በአግባቡ በመጠቀም፣ የተማረ የሰው ኃይል ዕውቀቱንና ቴክኖሎጂን ከሀገር በቀል ሀብት ጋር ካቀናጀ ማህበረሰቡ በሥራ መለወጥ እንደሚችል እነዚህ በሴቶች የሚመሩ ሥራ ፈጣሪ እህትማማቾችና አባታቸው በገሃድ ባሳዩት አርአያነት አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ ነው -ምሁራን

ጎንደር ፤ህዳር 2/2019 (ኢዜአ) ፡-የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን የዩኒቨ...

Nov 12, 2026

የአፍሪካ የልማት ተምሳሌቷ፡ዘላቂ መሠረተ ልማት እመርታ

አዲስ አበባ በለውጥ ጉዞዋ ውስጥ የጀመረችውን የከተማ ልማት እንቅስቃሴ ግለት ሳታስቀይር፣ የዘላቂ መሠረተ ልማት ግንባታዋን በማፋጠን ወደ ተቀናጀና ዘመናዊ ከተማ...

Nov 9, 2026

ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች ናቸው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች መሆና...

Oct 29, 2026

ሀብትን አውቆና አበልጽጎ ለትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር የመደመር መንግሥት ዋነኛ ዓላማ ነው - አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...

Oct 16, 2026