የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለአፍሪካ ዘላቂ የጤና ሥርዓት ግንባታ ትብብሯን ለማጠናከር ቁርጠኛ ናት

Nov 24, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ህዳር 14/2019 (ኢዜአ)፦ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለአፍሪካ ዘላቂ የጤና ሥርዓት ግንባታ ትብብሯን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሼክ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን ገለጹ።

5ኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ጉባኤው "የአፍሪካ የጤና ደህንነት እና ሉዓላዊነት፤ ከጤና ጥገኝነትና ተጋላጭነት ወደ ባለቤትነትና ጽናት የሚደረግ ሽግግር" በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

ይህ ዓመታዊ ጉባኤ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የሕዝብ ጤና ባለሙያዎች፣ ሳይንቲስቶች፣ የልማት አጋሮች፣ የግሉ ዘርፍ ተወካዮች እና የማኅበረሰብ አንቂዎች በአንድ መድረክ ተገናኝተው በአህጉሪቷ ቅድሚያ በሚሰጣቸው የጤና አጀንዳዎች የሚመክሩበት፣ ሳይንሳዊ ዕውቀቶችን የሚለዋወጡበት እንዲሁም አዳዲስ የፈጠራ መፍትሔዎችን የሚያስተዋውቁበት የትብብር ማዕቀፍ ነው።

በተጨማሪም ገለባኤው ትብብርን ለማጠናከር፣ ምርምርን ለማሳደግ እና የማይበገርና በራስ አቅም ላይ የተመረኮዘ የጤና ሥርዓት ለመገንባት የሚያስችሉ አፍሪካ-መር አካሄዶችን ለማጠናከር ሰፊ ዕድል ይፈጥራል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሼክ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር የአፍሪካ መሪዎች ለአህጉሪቱ የጤና ደኅንነት ግልጽ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ገልጸው እነዚህን ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ወደ ተግባር ለመቀየር በትብብር ለመሥራት ዝግጁ ነን ብለዋል።

እ.ኤ.አ. በ2017 የተባበሩት የአረብ ኢሚሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በአፍሪካ አህጉር ሞቃታማ አካባቢዎች ተላላፊ በሽታዎችን ለማጥፋት የሚያስችለውን 'Reaching the Last Mile Fund' የተሰኘ ፈንድ ማቋቋማቸውን ገልጸዋል።

እነዚህ በሽታዎች መከላከል የሚቻል የዓይን መታወርንና ዘላቂ የአካል ጉዳትን እያስከተሉ እንደነበር ገልጸው ማንኛውም ግለሰብ መከላከል በሚቻል በሽታ እንዳይሰቃይ የሚያስችል ተልዕኮን በመደገፍ አጋር መሆናችን ያስደስተናል ብለዋል።

የአንድ ሕፃን መወለድ የደስታ ቀን መሆን እንዳለበት ገልጸው እያንዳንዷ እናት እሷም ሆነች ልጇ የሚያስፈልጋቸውን የጤና እንክብካቤ እንደሚያገኙ በማረጋገጥ ልጇን እንድትቀበል ማድረግ የሁሉም የጋራ ሀላፊነት መሆኑን ጠቅሰዋል።

ይህንን ኃላፊነት ለመወጣት እንዲያግዝ እ.ኤ.አ. በሚያዝያ 2025 የመሐመድ ቢን ዛይድ የሰብዓዊነት ፋውንዴሽንና ሌሎች መሥራች ለጋሾች በአቡ ዳቢ ከአፍሪካ የጤና ሚኒስትሮች ጋር በመሰባሰብ 'The Beginning Fund' የተሰኘውን ፈንድ ለማስጀመር መወሰኑን አስታውሰዋል።

ይህ ፈንድ፣ በአፍሪካ አገራት የእናቶችንና የአራስ ሕፃናትን ሕይወት ለማዳን በተረጋገጡ ውጤታማ የጤና ጣልቃ ገብነቶች ላይ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የተባበሩት የአረብ ኢሚሬቶች ከፍተኛ መጠን ያለው የህክምና ቁሳቁስ እንዲሁም የክትባት ዶዞችን ለማጓጓዝ ድጋፍ ማድረጓን ጠቁመዋል።

የተባበሩት የአረብ ኢሚሬቶች በአፍሪካ አህጉር የመድኃኒቶችን ምርት ማሳደግ ለአፍሪካ ሕብረት ቅድሚያ በመስጠት የምትደግፈውና አብራ የምትሠራ መሆኑን አመላክተዋል።

ባለፈው ዓመት በማላቦ ከአፍሪካ ሕብረት ጋር የጤና ትብብር ስምምነት መፈረማቸውን አስታውሰው ይህ ስምምነት ጤናማ አፍሪካ ለሁላችንም የበለጸገ የወደፊት ዕጣ ፈንታ መሠረት ናት የሚለውን የጋራ እምነት እንደሚያንጸባርቅ ተናግረዋል።

ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የአፍሪካን የጤና ደኅንነት ለተባበሩት የአረብ ኢሚሬቶች ስትራቴጂካዊ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አድርገው እንደሚመለከቱት ተናግረዋል።

የተባበሩት የአረብ ኢሚሬቶች እንደ አጋር አፍሪካውያን አገራት ያስቀመጧቸውን ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች በተግባር ለመፈጸም አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ መርዳትና አብሮ መሥራት መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህም የጤና እንክብካቤ የሚሰጡ ተቋማትን፣ አስፈላጊ መድኃኒቶችን የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍና በኢንቨስትመንት በማጠናከር እንዲሁም ከአፍሪካ ልምዶችና ይህንን ሥራ ለቀጣይ ዓመታት ከሚመሩት ሰዎች በመማር አብሮ መሥራትን የሚያካትት መሆኑን ገልጸዋል።

ጉባኤው የአፍሪካን የጤና ሉዓላዊነት በማጠናከርና ለቀውሶች በተሻለ ሁኔታ ምላሽ መስጠት የሚችል፣ ለሕብረተሰቡም ለብዙ ትውልዶች የሚያገለግል የጤና ሥርዓት መገንባት የሚያስችል የተሳካ ጉባኤ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ ነው -ምሁራን

ጎንደር ፤ህዳር 2/2019 (ኢዜአ) ፡-የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን የዩኒቨ...

Nov 12, 2026

የአፍሪካ የልማት ተምሳሌቷ፡ዘላቂ መሠረተ ልማት እመርታ

አዲስ አበባ በለውጥ ጉዞዋ ውስጥ የጀመረችውን የከተማ ልማት እንቅስቃሴ ግለት ሳታስቀይር፣ የዘላቂ መሠረተ ልማት ግንባታዋን በማፋጠን ወደ ተቀናጀና ዘመናዊ ከተማ...

Nov 9, 2026

ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች ናቸው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች መሆና...

Oct 29, 2026

ሀብትን አውቆና አበልጽጎ ለትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር የመደመር መንግሥት ዋነኛ ዓላማ ነው - አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...

Oct 16, 2026