🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ህዳር 15/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ዓለም አቀፍ የግብርና ምርት ወጪ ንግድ ተወዳዳሪነትን እያጎለበተ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ያስሚን ወሃብረቢ ገለጹ።
15ኛው ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና ቅባት እህሎች ጉባኤ “የማይበገር ንግድና ዘላቂ የእሴት ሰንሰለቶች” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም መካሄድ ጀምሯል።
በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ጥራጥሬና ቅባት እህሎች ላኪዎች ማኅበር ትብብር የተዘጋጀው ጉባኤ ከዛሬ ሕዳር 15 እስከ 16/2019 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
በጉባኤው ላይ ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡና ከ600 በላይ አምራቾች፣ ላኪዎች፣ ዓለም አቀፍ ገዥዎች፣ የፋይናንስ ተቋማትን ጨምሮ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ያስሚን ወሃብራቢ በጉባኤው መክፈቻ፤ ባለፈው በጀት ዓመት ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች 11 ነጥብ 2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኝቷል ብለዋል።
በአጠቃላይ ከወጪ ንግድ ከተገኘው ገቢም የጥራጥሬና የቅባት እህሎች ዘርፍ ወደ 572 ነጥብ 9 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገደማ እንደሚሸፍን ተናግረዋል።
የጥራጥሬና የቅባት እህሎች የወጪ ንግድ ገቢ ያስገኘው እመርታም ከባለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር ትልቅ ውጤት የተገኘበት መሆኑን ተናግረዋል።
ይህም የግብርና ልማት ለብሔራዊ ኢኮኖሚና ለዓለም አቀፍ የምግብ አቅርቦት ሰንሰለት የሚያበረክተውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ የበለጠ ለማስፋት ያሉትን ዕድሎች እንደሚያጎላ አስረድተዋል።
የኢትዮጵያን የንግድ ኢንቨስትመንትና የምርት አቅርቦት ተመራጭነት ለማሳደግ የወጪ ንግድ አፈጻጸምን በተቋማዊ ጽናት፣ በምርት ጥራትና በገበያ ተወዳዳሪነት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።
የንግድ ትስስርና የጥራት ማሻሻያ ፖሊሲዎችን በመተግበርም ከደረጃዎች እስከ ተስማሚነት ምዘና፣ ከአክሬዲቴሽን እስከ ዕውቅና አሰጣጥ ያሉ ሁሉንም የጥራት መሠረተ ልማቶች በአንድ ቦታ የሚያሰባስብ ግዙፍ የጥራት መንደር ተገንብቶ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያም ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን፣ የጅምላና ችርቻሮ ንግድ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስፋት ለውጭ አልሚዎች ምቹ ዕድል መፍጠሩን ጠቅሰዋል።
ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ዓለም አቀፍ የግብርና ምርት ወጪ ንግድ ተወዳዳሪነትን እያጎለበተ መሆኑን አንስተዋል።
ይህም የኢትዮጵያን የገቢና ወጪ ንግድ፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰትና ተያያዥ ጉዳዮች በማሳለጥ ከፍተኛ ውጤት እያስገኘ መምጣቱን ገልጸዋል።
የፋይናንስ ዘርፍ የተወዳዳሪነት ዕድገትም የአገልግሎት ጥራትና ቅልጥፍናን በማስፋት ሁሉን አቀፍ የታክስ፣ የጉምሩክና የቁጥጥር ማሻሻያዎች አስቻይ የንግድና ኢንቨስትመንት ከባቢ ፈጥረዋል ብለዋል።
በጉባኤው የፖሊሲና ዓለም አቀፍ ገበያ አዝማሚያ፣ የገበያ መዳረሻዎች፣ የምርት ጥራት መስፈርቶችን ጨምሮ በመስኩ የሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎች ላይ ምክክር ይደረጋል።
ጉባኤው ኢትዮጵያ በጥራጥሬና ቅባት እህሎች ያላትን አቅም ማስተዋወቅ፣ በገዥዎችና ሻጮች መካከል ጠንካራ ግንኙነት እንዲፈጠር ማስቻል ከጉባኤው ግቦች መካከል ይገኝበታል።
በምርቶች ላይ እሴት መጨመር ያለውን ሁሉን አቀፍ ጠቀሜታ ማጉላትንም ጉባኤው አልሟል።
ጎንደር ፤ህዳር 2/2019 (ኢዜአ) ፡-የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን የዩኒቨ...
Nov 12, 2026
አዲስ አበባ በለውጥ ጉዞዋ ውስጥ የጀመረችውን የከተማ ልማት እንቅስቃሴ ግለት ሳታስቀይር፣ የዘላቂ መሠረተ ልማት ግንባታዋን በማፋጠን ወደ ተቀናጀና ዘመናዊ ከተማ...
Nov 9, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች መሆና...
Oct 29, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...
Oct 16, 2026