የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የሌማት ትሩፋት መርሃግብር የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ አድርጎናል 

Nov 26, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አርባ ምንጭ፤ ህዳር 16/2019(ኢዜአ)፦ የሌማት ትሩፋት መርሃግብር በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የገቢ ምንጭ በመሆን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዳደረጋቸው በአርባ ምንጭ ከተማ የመርሃግብሩ ተሳታፊዎች ገለጹ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የሌማት ትሩፋት መርሀግብር የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር የኢኮኖሚ ሉአላዊነቷን ያስከበረች ነጻ ሀገር እውን ለማድረግ ያለመ ነው።

በኢትዮጵያ የምግብ ምርትን ለማሳደግ፣ የዜጎችን የሥነ ምግብ አቅርቦት ለማሻሻል እና የሥራ ዕድል ለመፍጠር የተጀመረ ሀገራዊ የልማት መርሃ ግብር መሆኑም ይታወቃል።

በመርሀግብሩ ከተተገበረ ጀምሮ ዜጎች በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ ከማገዝ ባለፈ የገቢ ምንጫቸውን በማስፋት የኑሮ ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ እያስቻለ ይገኛል።

በአርባ ምንጭ ከተማ በመርሃግብሩ የተሳተፉ ተጠቃሚዎች ለኢዜአ እንደገለጹት፣ መርሀግብሩ የአመጋገብ ልምዳቸውን ከመቀየር ባለፈ በሥራ ዕድል ፈጠራ የገቢ ምንጭ እየሆናቸው መምጣቱን ተናግረዋል።


የርሆቦት የወተት ላም እርባታ ማህበር ሰብሳቢ ጮሎ ጾና እንዳሉት፣ መርሃ-ግብሩ እንደሀገር በተጀመረበት ወቅት ማህበራቸው በአራት የወተት ላሞች የእርባታ ሥራውን ጀምሯል።

መንግስት ለማህበሩ እርባታ የሚሆን ቦታ እና የገንዘብ ብድር ያመቻቸ ሲሆን ይህም በየጊዜው ድጋፍና ክትትል በማድረግ ውጤታማ አድርጎናል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት የላሞቹ ቁጥር ወደ 38 ከፍ ማለቱን ጠቅሰው ላሞቹ እያንዳንዳቸው በቀን ከ25 እስከ 37 ሊትር ወተት እንደሚሰጡ ገልጸዋል።

በዚህም ለከተማው ማህበረሰብ ወተት እያቀረቡ መሆናቸውን የገለጹት ጮሎ፣ በ218 ሺህ ብር ካፒታል የጀመሩት ሥራ በአሁኑ ወቅት ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ መድረሱን ተናግረዋል።

የ"ስንታ" ዶሮ እርባታ ማህበር ፀሐፊ ወጣት ነህሚያ ደባልቄ በበኩሏ፤ ማህበሩ ባለፈው ዓመት በ150 ዶሮዎች ሥራ መጀመሩን ገልጻለች።


በአሁኑ ወቅት 630 ዶሮዎችን እያረቡ መሆናቸውን ጠቅሳ በጫጩት፣ በዕንቁላልና በሥጋ ዶሮ ሽያጭ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸው እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።

የሌማት ትሩፋት መርሀግብር የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ ጤናማ ቤተሰብ እንዲኖረን አስችሎናል ያለችው የማህበሩ ፀሐፊ መንግስት በመስሪያ ቦታና በተለያየ መንገድ እያደረገላቸው ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርባለች።


መርሃ-ግብሩ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የሚደረገው ሽግግር እንዲሳካ ድርሻው የላቀ በመሆኑ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ያሉት ደግሞ ለመርሀግብሩ ተጠቃሚዎች ድጋፍ እያደረጉ ያሉት የግብርና ባለሙያ አቶ ሰለሞን ሞገስ ናቸው።

በመርሀግብሩ ዜጎች በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናቸውን በማረጋገጥ ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

የአርባምንጭ ከተማ ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ እያሱ አፈወርቅ፤ የሌማት ትሩፋት መርሃግብር በከተማዋ የምግብ ምርትን ከማሳደግ ባለፈ የቤተሰብ ገቢን እያጠናከረ መሆኑን ተናግረዋል።


በተጨማሪም ለዜጎች የሥራ እድልን በመፍጠርና የከተማውን ኢኮኖሚ በማነቃቃት ረገድ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑን ነው የገለጹት።

እንደ አቶ እያሱ ገለጻ በከተማው በወተት፣ በዶሮ፣ በሥጋ፣ በማርና በዓሣ ምርት ዘርፎች 44 መንደሮች ተቋቁመዋል።

በዘርፉ የተሠማሩ ማህበራትም ለበርካታ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ለከተማው ኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ ነው -ምሁራን

ጎንደር ፤ህዳር 2/2019 (ኢዜአ) ፡-የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን የዩኒቨ...

Nov 12, 2026

የአፍሪካ የልማት ተምሳሌቷ፡ዘላቂ መሠረተ ልማት እመርታ

አዲስ አበባ በለውጥ ጉዞዋ ውስጥ የጀመረችውን የከተማ ልማት እንቅስቃሴ ግለት ሳታስቀይር፣ የዘላቂ መሠረተ ልማት ግንባታዋን በማፋጠን ወደ ተቀናጀና ዘመናዊ ከተማ...

Nov 9, 2026

ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች ናቸው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች መሆና...

Oct 29, 2026

ሀብትን አውቆና አበልጽጎ ለትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር የመደመር መንግሥት ዋነኛ ዓላማ ነው - አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...

Oct 16, 2026