🔇Unmute
አዲስ አበባ፣ ህዳር 17/2019 (ኢዜአ)፦ የባለፉት ዓመታት ሪፎርሞች ኢኮኖሚው አይበገሬ ሆኖ እንዲቀጥል እና ሀገር እንዲጸና ወሳኝ ሚና መጫወቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በመደበኛ ጉባኤው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ያቀረቡትን የ2019 ዓ.ም የመንግሥት ዕቅድ መነሻ በማድረግ የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄና አስተያየቶቻቸውን አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለቀረቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ላይ በዓለም ያለው ፖለቲካዊ ውጥረት፣ ውድድር እና ፉክክር የንግድ ስርዓቱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩን ገልጸዋል።
በተዛባው የንግድ ስርዓት ውሰጥ ነዳጅ እና ማዳበሪያን ጨምሮ ወሳኝ በሚባሉ ምርቶች ላይ እጥረት መከሰቱን አመልክተዋል።
በምርት ማጋበስ ምክንያት በምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሬ መታየቱንም ተናግረዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የእድገት መንገራገጭ እንዳለ እና የኑሮ ወድነት ጫና መጨመሩንም ነው የገለጹት።
በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ መንግሥት ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተገበራቸው ሪፎርሞች ኢኮኖሚው አይበገሬ ሆኖ እንዲቀጥል እና ሀገር እንዲጸና ማስቻሉን አመልክተዋል።
ጎንደር ፤ህዳር 2/2019 (ኢዜአ) ፡-የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን የዩኒቨ...
Nov 12, 2026
አዲስ አበባ በለውጥ ጉዞዋ ውስጥ የጀመረችውን የከተማ ልማት እንቅስቃሴ ግለት ሳታስቀይር፣ የዘላቂ መሠረተ ልማት ግንባታዋን በማፋጠን ወደ ተቀናጀና ዘመናዊ ከተማ...
Nov 9, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች መሆና...
Oct 29, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...
Oct 16, 2026