የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የጎዴ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥር እየተከናወነ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Nov 27, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፣ ህዳር 17/2019 (ኢዜአ)፦የጎዴ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥር እየተከናወነ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ዛሬ 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በመደበኛ ጉባኤው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ያቀረቡትን የ2019 ዓ.ም የመንግሥት ዕቅድ መነሻ በማድረግ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማብራሪያቸው እንደገለጹት፤ በሶማሌ ክልል በጎዴ እየተገነባ ያለው የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ በከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥር እየተከናወነ ነው።

የተመረጠው ቦታ በጣም አለታማ በመሆኑ ላለፉት ጥቂት ወራት ሲከናወን የቆየው የቦታ ዝግጅት ሥራ ከሞላ ጎደል እየተጠናቀቀ ይገኛል ብለዋል።

ፕሮጀክቱ ለሠራተኞቹ ብቻ 18 ሺህ መኖሪያ ቤቶችን በመገንባት አንድ ከተማ የመገንባት ያህል ሥራ እንደሚሠራ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

የቤት ግንባታ ግብዓቶችንና ግዙፍ ማሽነሪዎችን ከውጭ በማስገባት ወደ ጎዴ ለማጓጓዝ በቂ የመንገድና የአስፋልት መሠረተ ልማት አለመኖር ፈተና ቢሆንም፣ ላሙን ጨምሮ በአካባቢው የሚገኙ ወደቦችን በመጠቀም ብዙ ማሽነሪዎችና የግንባታ ማቴሪያሎች መግባታቸውን አስረድተዋል።

የማዳበሪያ ፋብሪካው አንድ ፋብሪካ ብቻ ሳይሆን የአሞኒያ፣ የዩሪያ፣ የግራኑሌሽን እና የከረጢት ማሸጊያ ፕላንቶችን እንዲሁም ከጋዝ ማውጫ እስከ ጎዴ የሚዘልቅ የፓይፕ ላይን ዝርጋታንና ማዳበሪያውን አሽገው ወደ ክልሎች የሚያሠራጩ ወደ 500 የሚጠጉ ትራኮችን ያካተተ ከሦስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት መሆኑን ገልጸዋል።

ምንም ዓይነት የተለየ አደጋ ወይም ችግር ካላጋጠመ በስተቀር በተያዘለት ጊዜ ከሚጠናቀቁ ሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል የጎዴ ማዳበሪያ ፋብሪካ አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ፕሮጀክቱ ለኢትዮጵያ እጅግ ወሳኝ በመሆኑ በየቀኑ የሚያጋጥሙ ችግሮችን እየፈቱ በተባለው ጊዜ ለማድረስ ጥረት እየተደረገ መሆኑንና የምክር ቤቱም ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ ነው -ምሁራን

ጎንደር ፤ህዳር 2/2019 (ኢዜአ) ፡-የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለዘላቂ የምጣኔ ሃብት እድገትና ለብሔራዊ ደህንነቷ መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን የዩኒቨ...

Nov 12, 2026

የአፍሪካ የልማት ተምሳሌቷ፡ዘላቂ መሠረተ ልማት እመርታ

አዲስ አበባ በለውጥ ጉዞዋ ውስጥ የጀመረችውን የከተማ ልማት እንቅስቃሴ ግለት ሳታስቀይር፣ የዘላቂ መሠረተ ልማት ግንባታዋን በማፋጠን ወደ ተቀናጀና ዘመናዊ ከተማ...

Nov 9, 2026

ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች ናቸው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በካፒታል ገበያ ዘርፍ ተቋማዊ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኞች መሆና...

Oct 29, 2026

ሀብትን አውቆና አበልጽጎ ለትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር የመደመር መንግሥት ዋነኛ ዓላማ ነው - አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ያሉትን ሀብቶች አውቆና አበልጽጎ ለተከታዩ ትውልድ የሚተርፍ ወረት መፍጠር መሆኑን የኢፌ...

Oct 16, 2026