
ደብረማርቆስ ፤ ሰኔ 16/2017 (ኢዜአ) ፡- በምሥራቅ ጎጃም ዞን ለመኸሩ እርሻ በግብአትነት የሚያስፈልገው የአፈር ማዳበሪያ ወቅቱን ጠብቆ ለአርሶ አደሩ በመቅረቡ የዘር ስራውን ለማቀላጠፍ ምቹ መደላድል መፍጠሩ ተገለጸ።
በምሥራቅ ጎጃም ዞን በ2017/2018 የምርት ዘመን 645ሺህ ሄክታር መሬት በማረሰ ከ25 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታውቋል።
ለምርት ዘመኑ እስካሁን ከ642ሺህ ኩንታል የሚበልጥ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ እንዲሰራጭ መደረጉም ተመልክቷል።
በዞኑ ከጎዛምን ወረዳ አርሶ አደሮች መካከል የኔሰው ታደሰ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በዚህ ዓመት የሚፈልጉትን ያህል የምርት ማሳደጊያ ግብዓት በወቅቱ በማግኘታቸው ለሰብል ልማቱ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።
ከአራት ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ መግዛታቸውን ገልፀው መሬታቸውን በገብስና በበቆሎ ዘር መሸፈናቸውን ተናግረዋል፡፡
ሌላኛው የዚሁ ወረዳ አርሶ አደር ልጅአለም ተሻገር፤ በዚህ ዓመት የማዳበሪያ እጥረትም ሆነ መዘግየት አለማጋጠሙን ተናግረዋል።
የሚያስፈልጋቸውን ያህል የአፈር ማዳበሪያ ተጠቅመው የእርሻ ማሳቸውን በወቅቱ በበቆሎ ዘር በመሸፈናቸው ምርታቸውን እንደሚያሳድግላቸው የሚጠብቁ መሆኑን አስረድተዋል።
አርሶ አደሮቹ እንደገለጹት፤ ለመኸሩ የእርሻ ወቅት ምርታማነትን ለማሳደግ በግብአትነት የሚያስፈልገውን የአፈር ማዳበሪያ ወቅቱን ጠብቆ በመቅረቡ የዘር ስራውን ለማቀላጠፍ ምቹ መደላድል ፈጥሯል።
በምሥራቅ ጎጃም ዞን ለምርት ዘመኑ ለአምራቹ የሚያቀርቡ የህብረት ስራ ማህበራት ከደረሰው 810 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ ከ642ሺህ ኩንታል የሚበልጥ ለአርሶ አደሩ እንዲሰራጭ መደረጉን በዞኑ ግብርና መምሪያ የግብአት አቅርቦት የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ኃይለኢየሱስ ዳምጤ አስታውቀዋል።
የእርሻው ስራውና የማዳበሪያ አቅርቦቱ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቅሰው፤ በዘመኑ የእርሻ ሰራ ላይ ከ350ሺህ በላይ አርሶ አደሮች በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
በምሥራቅ ጎጃም ዞን በ2017/2018 የምርት ዘመን 645ሺህ ሄክታር መሬት በማረሰ ከ25 ሚሊዮን በላይ ምርት ለማግኘት መታቀዱን ያመለከቱት የስራ ሂደቱ አስተባባሪ፤ እቅዱን ለማሳካት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
ከእቅዱ ውስጥ እስካሁን 525ሺህ ሄክታር መሬት መታረሱንና ከዚህም 129 ሺህ ሄክታሩ በተለያየ የሰብል ዘር መሸፈኑን አስታውቀዋል።
የግብርና መምሪያው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ በ2016/2017 የምርት ዘመን 609ሺህ ሄክታር ታርሶ በተለያየ የሰብል ዘር ከለማው መሬት ከ22 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ተገኝቷል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026