የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

የኢኮኖሚ ሪፎርሙ በሀገር በቀል እውቀት የተቃኘ እና በራስ ባለቤትነት የሚመራ ነው- እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

Apr 15, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተተገበረ የሚገኘው የኢኮኖሚ ሪፎርም በሀገር በቀል እውቀት የተቃኘ እና በራስ ባለቤትነት የሚመራ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገለጹ።

የ2026 የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የዓለም ባንክ የፀደይ ወቅት ስብሰባ በዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ከስብሰባው ጎን ለጎን በተዘጋጀ የልማት አቅም ግንባታ መድረክ ላይ ተሳትፈዋል።

እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያን አጠቃላይ የፋይናንስ ዘርፍ ማሻሻያ አጀንዳ ለከፍተኛ የዓለም አቀፍ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች አብራርተዋል።

በስብሰባው ላይ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ፣ ከዓለም ባንክ እና ከአውሮፓ ኮሚሽን የተወከሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የባንኩ ገዥ "ገበያዎችን፣ተቋማትን እና መረጋጋትን በፈታኝ ወቅቶች ውስጥ መገንባት" በሚል መሪ ርዕስ በሰጡት ገለጻ፤ በኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ አማካኝነት በፋይናንስ ሥርዓቱ ላይ እየተከናወነ ያለውን መዋቅራዊ ሽግግር በዝርዝር አቅርበዋል።

በዚህም ዘርፉን ለማዘመን እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን ለተሳታፊዎች አስረድተዋል።


የባንኩ ገዥ ኢትዮጵያ ወደ ወለድ ተመን ተኮር የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ እያደረገች ያለውን ሽግግር እና በገበያ የሚወሰን የውጭ ምንዛሬ ተመን ሥርዓት ትግበራን በዋናነት አንስተዋል።

በተጨማሪም በአዲሱ የብሔራዊ ባንክ አዋጅ እና በዘመናዊ የባንክ ሥራ ሕግጋት የታገዘው የቁጥጥር ማዕቀፍ፣ የሀገሪቱን የፋይናንስ መዋቅር ሙሉ በሙሉ እየለወጠው እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የገዢው መልዕክት ዋነኛ ማጠንጠኛም የሪፎርም ባለቤትነት ሲሆን፤ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በሀገር በቀል እውቀት የተቃኙ እና በስትራቴጂያዊ ቅደም ተከተል የሚመሩ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

ከተለያዩ አካላት የሚገኘው ማንኛውም የቴክኒክ ድጋፍም ቢሆን በሀገሪቱ ፍላጎት ላይ የተመሠረተና ከልማት የቅድሚያ ትኩረቶች ጋር የተጣጣመ እንጂ ከውጭ ተጽዕኖ የሚመነጭ አለመሆኑን አስገንዝበዋል።

ወደፊት ስለሚከናወኑ ተግባራት ማብራሪያ የሰጡት የባንክ ገዥው፤ በቀጣዩ ምዕራፍ የሀገር ውስጥ የፋይናንስ ገበያን ይበልጥ ማሳደግ እና ዘርፉን ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ማድረግ የሪፎርሙ ቀዳሚ አጀንዳዎች መሆናቸውን አመልክተዋል።

ለዚህም ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት ተከታታይነት ያለው የተቋማት አቅም ግንባታ፣ የፖሊሲ ቀጣይነት እና የግል ዘርፉን የሚመራውን ኢኮኖሚ መሸከም የሚችል ጠንካራ የፋይናንስ ሥርዓት መገንባት ወሳኝ መሆኑን መግለጻቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሻሻል የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ

እምድብር፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ):- የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታ...

Jul 27, 2026

በጌዴኦ ዞን ከ44 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ወደ ተግባር ተገብቷል

ዲላ፤ ሐምሌ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በጌዴኦ ዞን በ2018/19 የመኸር አዝመራ ወቅት ከ44 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ትግበራ መገባቱን...

Jul 21, 2026

ከአፍሪካ ትልሞች ጋር የተሳሰረው የኢትዮጵያ ሜጋ ፕሮጀክቶች ስኬት

ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚዎች በአፍሪካ የነጻነት ትግል ግንባር ቀደም በመሆን፣ የቅኝ ግዛት ቀንበርን በመስበር ለቀሪው አህጉር የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀች ሀገር ና...

Jun 27, 2026

በኦሮሚያ ክልል የተከናወኑ የመስኖ ልማት ሥራዎች ዜጎችን ከተረጂነት አውጥተዋል

ሮቤ፣ሰኔ 18/2018(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል የአርሶና አርብቶ አደሩን የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስ የተከናወኑ የመስኖ ልማት ሥራዎች ዜጎችን ከተረጂነት በማውጣ...

Jun 26, 2026