የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

በከተማ አስተዳደሩ ከ36 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደዋል

May 12, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህር ዳር ፤ግንቦት 3/2018 (ኢዜአ)፡-በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከ36 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን የከተማ አስተዳደሩ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ገለፀ።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመምሪያው ኃላፊ ብርሃን ንጉሴ ለኢዜአ እንዳሉት፤በከተማዋ የኢንቨስትመንት ዘርፉን በተቀናጀ አግባብ ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታማ ናቸው ።

ባለፉት ዘጠኝ ወራትም 320 አዳዲስ ባለሃብቶች መዋለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደዋል ብለዋል።

ባለሃብቶቹ ከ36 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ሲሆን ወደ ስራ ሲገቡም ከ19 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ እድል የመፍጠር አቅም እንዳላቸው ተናግረዋል።

ባለሃብቶቹ ፈጥነው ወደ ስራ እንዲገቡ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አንስተው፤ በዚህ ዓመትም መስፈርቱን ለሚያሟሉ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች 102 ሄክታር መሬት መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

በከተማው ቀደም ሲል የኢንቨስትመንት ቦታ ወስደው ተደጋጋሚ እገዛና ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ስራ ያልገቡ 24 ባለሃብቶችም የወሰዱትን ቦታ እንዲመልሱ መደረጉንም አስታውቀዋል።

በከተማዋ በኮሪደር ልማት የተከናወኑት ተግባራት ለኢንቨስትመንት ይበልጥ ተመራጭ እንድትሆን ያደረጉ ሲሆን በተለይ በአገልግሎትና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ መሰማራት ለሚፈልጉ ምቹ ሁኔታ እንዳለ አመልክተዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ኢንቨስትመንትን ከማሳደግ ጎንለጎንም ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተካሔደ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ 23 ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት እንዲገቡ ማድረጉን ገልፀዋል።


በዚህም ከ 3 ሺህ 800 ለሚበልጡ ወገኖች የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉንም ገልፀዋል

በ98 ኢንዱስትሪዎችም 155 ነጥብ 6 ቶን ተኪ ምርት በማምረት ከ118 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን እንደተቻለ አስረድተዋል።

ዘጠኝ አምራች ኢንዱስትሪዎች 17 ነጥብ 7 ቶን የተለያዩ ምርቶችን ወደ ውጭ ሃገራት ገበያ በመላክ 22 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል ነው ያሉት።


የኢትዮጰያ ታምርት ንቅናቄ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅምም ከ59 በመቶ ወደ 63 በመቶ ከፍ ማድረግ እንዳስቻለም አስገንዝበዋል።

በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማሩ 287 ኢንዱስትሪዎች እንዳሉም የመምሪያ ኃላፊዋ ጨምረው አስታውቀዋል።


የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026

በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ ናቸው 

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...

Aug 7, 2026