🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ታዳጊዎች ልዑክ በዓለም አቀፉ የታዳጊዎች የሮቦቲክስና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ሻምፒዮና በመሳተፍ በህዝብ ምርጫ ሽልማት ዘርፍ 1ኛ በመሆን አጠናቋል፡፡
በሚቺጋን አሜሪካ ሎውረንስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው የ2026 የሮቦፌስት ዓለም አቀፍ የታዳጊዎች የሮቦቲክስና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ሻምፒዮና ኢትዮጵያዊያን ተወዳዳሪዎች አስደናቂ ድሎችን አስመዝግበዋል።
ዘንድሮ በተካሄደው ውድድር (Robofest 2026 International Championships) ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች ከ39 የቴክኖሎጂ ሀያላን ሀገራት ከተወጣጡ 738 ቡድኖች ጋር በመፎካከር ነው በተለያዩ ዘርፎች ማሸነፍ የቻሉት፡፡
በውድድሩ በህዝብ ምርጫ ሽልማት ዘርፍ ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች ቀዳሚ በመሆን ሲያሸንፉ፥ በህክምና ሮቦቲክስ ዘርፍ 5ኛ እንዲሁም በፈጠራ ማሳያ 6ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡
ከአንድ ወር በፊት በግሪክ በተካሄደው ዓለም አቀፍ ሚኖአን ሮቦቲክስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች 2ኛ ደረጃን በማግኘት የሀገራቸውን ስም ማስጠራታቸው የሚታወስ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026