የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማሳለጥ የዲጂታልና ቴክኖሎጂ ክህሎት ልማት ውጤታማነትን ማስፋት ይገባል

May 20, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማሳለጥ የዲጂታልና ቴክኖሎጂ ክህሎት ልማት ውጤታማነትን ማስፋት እንደሚገባ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስገነዘበ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን በ22ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ገምግሟል።


የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርታቸው፤ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የአንገብጋቢ ችግሮች መፍቻ ቁልፍ መሳሪያ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያን የዲጂታል ልማት ለማሳለጥም የ10 ዓመት መሪ ዕቅድና ከዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የቀጠለ የዲጂታል ኢትዮጵያ-2030 ስትራቴጂ በመቅረፅ ውጤታማ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በክህሎት ልማትና በስታርት አፕ፣ በሮቦቲክስና ሳይበር ደኅንነት፣ በስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል፣ በጥናትና ምርምር፣ በዲጂታል ግብይት፣ በጥናትና ምርምር ከፍተኛ ውጤት እየተገኘ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም የመሶብ አንድ ማዕከል የዲጂታል አገልግሎት ለዜጎች የመንግስትን አገልግሎት በማሳለጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ አንስተዋል።

የምክር ቤቱ አባላትም፤ በመንግሥት አገልግሎቶች፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ የፈጠራ ውጤታማነትና ቀጣይ አቅጣጫን አስመልክቶ ጥያቄና አስተያየት አቅርበዋል።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፤ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ የቴክኖሎጂ ዕውቀት ለማሳደግ ተቋማትን የሚደግፍ ካውንስል ተዋቅሮ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ በሀገሪቱ ጠረፋማ አካባቢዎች የሃይል እና የኢንተርኔት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ተቋሙ ራዕይ አንግቦ እየሰራ እንደሆነም ገልጸዋል።

በቀጣይም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ የዲጂታል ሽግግር ለማፋጠን የተፈጠረውን አስቻይ የፈጠራና ክህሎት ልማት ምኅዳር የበለጠ በማጠናከር ውጤታማ ሥራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።


በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር)፤ የዲጂታል ልማት የኢኮኖሚ ዕድገት ማሳለጫ መሳሪያ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያን የዲጂታል ልማትና ሽግግር ለማፋጠን የተዘረጉ አስቻይ የአሰራር ምኅዳሮችም ውጤት በማምጣት የዜጎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በተለይም የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና የዜጎችን የፈጠራ ክህሎትና ዕውቀት በማበልፀግ አይነተኛ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ አንሰተዋል።

በቀጣይም የኢትዮጵያን የዲጂታል ሉዓላዊነት በማረጋገጥ ሁለንተናዊ ብልፅግናን የሚያረጋግጥ የፈጠራና ክህሎት ልማት ሥራዎች የበለጠ ሊጠናከሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026

በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ ናቸው 

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...

Aug 7, 2026