የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

የኢትዮጵያ የመሠረተ-ልማት ጉዞ በትጉህና ግልጽ መርሆዎች እና በተዋቀረ አፈጻጸም ወደሚመራ የለውጥ ዘመን ተሸጋግሯል

Jun 24, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ሰኔ 16/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የመሠረተ-ልማት ጉዞ ለዘመናት ከዘለቀው ሀገራዊ ትልም ተነሥቶ አሁን ላይ በትጉህና ግልጽ መርሆዎች እንዲሁም በተዋቀረ አፈጻጸም ወደሚመራ የለውጥ ዘመን መሸጋገሩንየኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት “ከለውጥ ወደ ዘላቂ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል የ“ኢትዮጵያ ታከናውናለች” ጉባኤ በመካሄድ ላይ ነው።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ በሰጡት ማብራሪያ፣ የኢትዮጵያ የመሠረተ-ልማት ጉዞ ለዘመናት ከዘለቀው ሀገራዊ ትልም ተነሥቶ አሁን ላይ በትጉህና ግልጽ መርሆዎች እንዲሁም በተዋቀረ አፈጻጸም ወደሚመራ የለውጥ ዘመን ተሸጋግሯል ብለዋል፡፡

ለዚህ ስኬት ደግሞ የለውጡ መንግሥት ሀገራዊ ተስፋን ከተቋማዊ አቅም ጋር ወደሚያጣጥም፣ ይበልጥ አመቺ፣ ቅደም ተከተላዊ እና የፋይናንስ ሥነ-ሥርዓትን ወደ ተከተለ አካሄድ ቁርጠኛ ሽግግር ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህም መሠረተ ልማትን ወደ ቀጣይነት ያለው ሀገራዊ እሴት እና ለትውልድ ተሻጋሪ ሀብት እንዲቀየር እያደረገው ይገኛል ነው ያሉት።

‎የንጹሕ ኢነርጂ፣ የዲጂታል ማስፋፊያ፣ የትራንስፖርት፣ የኮንስትራክሽን እና የአረንጓዴ ቴክኖሎጂ ስትራቴጂካዊ ዘርፎች ሀገሪቱ የምታደርገውን የለውጥና የብልጽግና ጉዞ እየመሩት መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ዕድገቷ ራሱን ችሎ የሚቀጥልና ለውጥ የሚያመጣበት ደረጃ ላይ ለመድረስ በትጋት እየገነባች ትገኛለች ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026

በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ ናቸው 

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...

Aug 7, 2026