🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 20/2018 (ኢዜአ)፦ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተመራቂዎች የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞ ለማፋጠን ዕውቀታቸውን ወደ ፈጠራ ማሸጋገር እንዳለባቸው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተርና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ ትዕግሥት ሀሚድ ገለጹ።
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ ምረቃ፣ በድህረ ምረቃ እና በሦስተኛ ዲግሪ በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 246 ተማሪዎች አስመርቋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተርና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ ትዕግሥት ሀሚድ ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞ ዳር ለማድረስ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ባለሙያዎችን ማፍራት ያስፈልጋል ብለዋል።
ሀገሪቱ አሁን ካለችበት የኢኮኖሚና የቴክኖሎጂ ደረጃ ከፍ እንድትል የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተመራቂዎች ሚና ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
የዛሬ ተመራቂ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ያገኙትን ዕውቀት ወደ ፈጠራና ወደ ኢንዱስትሪ ምርታማነት አቅም እንዲቀይሩ በማስገንዘብ ሀገራቸውን በቅንነት እንዲያገለግሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ በበኩላቸው፤ ባለፉት ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ሰፊ ሥራ መሠራቱን ተናግረዋል።
ትምህርት ግቡን እንዲመታ ከተደራሽነቱ ባሻገር ጥራቱን ማረጋገጥ የግድ መሆኑን ጠቅሰው፥ መንግሥት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ብቁና ተመራማሪ ትውልድ ለማፍራት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ሪፎርም አድርጎ ወደ ሥራ መግባቱን አብራርተዋል።
በዚህም ሳይንስና ቴክኖሎጂን ጨምሮ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ ረገድ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን ነው የገለጹት።
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ደረጄ እንግዳ (ዶ/ር)፤ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ሲያስመርቅ የዘንድሮው ለ12ኛ ጊዜ መሆኑን ገልጸዋል።
ዩኒቨርሲቲው የኢትዮጵያን የልማት ግቦች ለማሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
ተመራቂ ተማሪዎች በተግባር ተኮር የቴክኖሎጂ ፈጠራና በኢንዱስትሪዎች ውስጥ በሚታዩ ተጨባጭ ችግሮች ላይ ያተኮሩ ችግር ፈች የምርምር ሥራዎችን ማከናወናቸውን አመላክተዋል።
ዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማሳለጥ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን በእጅጉ እያሳደገ እንደሚገኝ አንስተዋል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026