🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2018(ኢዜአ)፦ በበጀት ዓመቱ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ስኬታማ ሥራዎች የታቀዱ ግቦችን ከማሳካት ባለፈ፣ ለዘርፉ ዕድገት ትልቅ አቅም የፈጠሩ መሆናቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመሆን የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸምን እየገመገመ ይገኛል።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፤ በበጀት ዓመቱ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና በተጠሪ ተቋማቱ የተመዘገበው የዕቅድ አፈጻጸም እጅግ ከፍተኛና ስኬታማ እንደነበር አብራርተዋል።
በርካታ ሀገራዊ ሥራዎችም በዓመቱ ለማሳካት ከታቀደው በላይ የላቀ ስኬት እንደተመዘገበባቸው ጠቁመዋል።

ተቋማዊ ሪፎርም በስኬት መከናወኑን ጠቅሰው ለሠራተኞች ምቹ የሆነ የሥራ ከባቢ ከመፍጠር በኩልም አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን ጠቁመዋል፡፡
በተለይም የተቋሙን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የተከናወኑ የአቅም ግንባታ ሥራዎች ውጤታማ መሆናቸውን አንስተው፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ተጠሪ ተቋማቱ የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል ሥርዓት ማሸጋገር መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡
በዚህም መሠረት ከንግድ ፈቃድ፣ ምዝገባ፣ ማሻሻያ እና ማደስ ጋር የተያያዙ ከ3 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ አገልግሎቶችን በኦንላይን መስጠት ተችሏል ብለዋል።
የንግድ ሥርዓቱን ማዘመንና የወጪ ንግድን ማሳደግን በተመለከተም ዘርፈ ብዙ ሥራዎች መከናወናቸውን ያነሱት ሚኒስትሩ፤ እነዚህ ስኬቶች ሀገሪቱ በበጀት ዓመቱ ከወጪ ንግድ ለማግኘት ያቀደችውን የ10 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር ገቢ ግብ ለማሳካት የሚያስችሉና ትልቅ አቅም የፈጠሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ዘመናዊ የግብይት ማዕከላትን በማስፋፋት በኩል አበረታች ሥራዎች መከናወናቸውንና በአሁኑ ወቅት የማዕከላቱ ቁጥር ከ31 በላይ መድረሱን ተናግረዋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞም የ10 ሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት የግብይት ማዕከላት ግንባታ የተጀመረ ሲሆን፣ ሁለቱ ተጠናቀው በበጀት ዓመቱ ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን አስታውቀዋል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026