የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

የአዲስ አበባ ከተማ ዓመታዊ ገቢ የመሰብሰብ አቅም 350 ቢሊዮን ብር ደርሷል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Jul 13, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባን ገቢ አሰባሰብ በማዘመን የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ዓመታዊ የገቢ የመሰብሰብ አቅም 350 ቢሊዮን ብር ገቢ ማድረስ እንደተቻለ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል።


ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉባኤው ላይ የከተማ አስተዳደሩን የ2018 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እያቀረቡ ነው።

በገቢ አሰባሰብ ሪፖርታቸው፤ መዲናዋ ከአፍሪካ ስድስት ታላላቅ ከተሞች ጋር በተደረገ ዝርዝር ጥናት፣ በበጀት አጠቃቀምና ለዘላቂ ልማት በማዋል ረገድ ቀዳሚ ሆና መመረጧን ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት በ2013 በጀት ዓመት 51 ቢሊዮን ብር የነበረው የከተማዋ ገቢ በ2018 በጀት ዓመት ወደ 350 ቢሊዮን ብር ማደጉን አስታውቀዋል።

በበጀት ዓመቱም ለመሰብሰብ በዕቅድ የተያዘውን ግብ 100 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ አስረድተዋል።

የዘንድሮው የገቢ አሰባሰብ ከ2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ116 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ብልጫ እና የ50 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን በሪፖርቱ አመላክተዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የገቢ አቅሙን ለማሳደግም የፍትሐዊነት መርህን በተከተለ መልኩ እንዲሰበሰብ በሰፊው መሠራቱን አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026

በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ ናቸው 

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...

Aug 7, 2026