የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

በጌዴኦ ዞን ከ44 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ወደ ተግባር ተገብቷል

Jul 21, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ዲላ፤ ሐምሌ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በጌዴኦ ዞን በ2018/19 የመኸር አዝመራ ወቅት ከ44 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ትግበራ መገባቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገለጸ።

በመኸር አዝመራው ከሚለማው መሬት ከ7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱም ተመልክቷል።


በዞኑ የመኸር አዝመራ ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ በመኸር እርሻ ወቅት ሊለማ የሚችልን መሬት ወደ ልማት በማስገባት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ይሠራል ብለዋል።

በተለይም መሬትን ደጋግሞ በማረስና የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሻሻል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት ተሠርቷል ነው ያሉት።

ዞኑ ከቡናና ከሌሎች ቋሚ ሰብሎች ጎን ለጎን በተያዘው መኸር ፈጥነው የሚደርሱና የምግብ ዋስትና ክፍተትን የሚሸፍኑ ሰብሎችም እንደሚለሙ ገልጸዋል።

ለዚህም ምርጥ ዘርና ማዳበሪያን ጨምሮ የግብዓት ስርጭት በወቅቱ እንዲከናወን ከማድረግ ባለፈ አርሶ አደሩ በኩታ ገጠም እንዲያለማም የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።

የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ተገኝ ታደሰ በበኩላቸው፣ በመኸር አዝመራው 44 ሺህ 715 ሄክታር መሬት በሰብል ለማልማት ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል።


ከዚህ ውስጥም 26 ሺህ 158 ሄክታር መሬት በአዝዕርት፣ አትክልትና ስራስር ሰብሎች የሚለማ ሲሆን በተለይ ገብስ፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ አተር፣ ባቄላና ድንች ዋና ዋናዎቹ ናቸው ብለዋል።

የተቀረው በእንሰትና ፍራፍሬ የሚሸፈን መሆኑን አንስተው በአጠቃላይ ከተያዘው የመኸር አዝመራ ከ7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን ተናግረዋል።

እቅዱን ለማሳካት የማሳ ዝግጅትና የግብዓት ስርጭት መከናወኑን አንስተው በየደረጃው የሚገኝ የግብርና አመራርና ባለሙያ በቅንጅት እየሠሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በንቅናቄ መድረኩ የዞንና የሁሉም ወረዳዎች አስተዳዳሪዎች፣ የዘርፉ የሥራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026

በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ ናቸው 

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...

Aug 7, 2026