የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

በምእራብ ጎንደር ዞን ከ22 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል

Jul 22, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ገንዳውኃ፤ ሐምሌ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በምዕራብ ጎንደር ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ22 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን የዞኑ ሥራና ክህሎት መምሪያ አስታወቀ።

​የመምሪያ ኃላፊ አቶ ኤፍሬም ወርቁ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የወጣቶችን የሥራ አጥነት ችግር በማቃለል በኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲችሉ የማድረግ ስራ ተሰርቷል።

​በዚህም በበጀት ዓመቱ በዞኑ የሚገኙ ጸጋዎችን በመለየት ከ22 ሺህ 500 በላይ ወጣቶች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል።

የስራ እድል የተፈጠረላቸው ዜጎች በኮንስትራክሽን፣ በእንጨትና ብረታ ብረት ስራ፣ በአገልግሎት ፣ በከብት ማድለብ፣ በወተት ልማትና ንብ ማነብን ጨምሮ በሌሎች የግብርና ዘርፎች መሰማራታቸውን ገልፀዋል።

የስራ እድሉ የተፈጠረላቸው ዜጎች 267 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የመስሪያ ካፒታል በብድር እንዲያገኙ ከማድረግ ባለፈም ለማምረቻና ለመሸጫ የሚሆኑ ከ700 በላይ ሼዶችና ኮንቲነሮችን ማስረከብ መቻሉን አስረድተዋል።

በቀጣይም የዞኑን እምቅ ጸጋዎች በሚገባ ለይቶ በመጠቀም ለወጣቱ የተሻለ የሥራ ዕድል ለመፍጠር በቁርጠኝነት እንደሚሠራ አስገንዝበዋል።

​በዞኑ በከብት ማድለብ ስራ የተሰማራው ወጣት ይስማው አቡዬ ፤በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተመቻቸለት የከብት ማድለብ ሥራ ከ300 ሺህ ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ማግኘት መቻሉን ነው የተናገረው።

በዚህም ከራሱ አልፎ ቤተሰቦቹን ለመደገፍ እንደቻለ አመልክቶ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

በዘላቂ ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ በእጣንና ሙጫ ማምረት ስራ የተሰማራው ወጣት አይሸሽም አለሙ በበኩሉ፤ ከ100 ባለይ ሆነው በመደራጀት በዘርፉ ባገኙት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጿል።

በበጀት ዓመቱ እጣንና ሙጫ በማምረትና ለገበያ በማቅረብ እያንዳንዳቸው ከ200 ሺህ ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን ነው ያስታወቀው።

በአሁኑ ወቅትም የተፈጥሮ ደኑ እንዲጠበቅ በጋራ ሆነው እየሰሩ መሆኑንም አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026

በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ ናቸው 

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...

Aug 7, 2026