የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

ግብርን በአግባቡና በወቅቱ በመክፈል የሚጠበቅብንን ሀገራዊ ግዴታ እየተወጣን ነው

Jul 29, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሀረር ፤ሐምሌ 21/2018(ኢዜአ)፦ ግብርን በአግባቡና በወቅቱ በመክፈል ሀገራዊ ግዴታቸውን እየተወጡ መሆኑን የሐረሪ ክልል ግብር ከፋዮች ተናገሩ።

የሐረሪ ክልል ታማኝ ለሆኑና ግብራቸውን በወቅቱ በመክፈል ላይ ላሉ ነጋዴዎች እውቅና ሰጥቷል።

ኢዜአ ያነጋገራቸው ግብር ከፋዮች እንዳሉት ግብርን በአግባቡና በወቅቱ በመክፈል የሚጠበቅባቸውን ሀገራዊ ግዴታ እየተወጡ ነው።

ከክልሉ ታማኝ ግብር ከፋዮች መካከል በአይን ህክምና ስራ ላይ የተሰማሩት ዶክተር ኑረዲን አብዲ እንዳሉት፤ የሚጠበቅብኝን ግብር በወቅቱ በመክፈሌ የተሰጠኝ እውቅና ለበለጠ ስራ የሚያነሳሳ ነው።

ከነጋዴው የሚሰበሰበው ግብር ለአካባቢው ልማት መፋጠን የሚውል በመሆኑም ስራዎችን በማሳደግ ለሀገር እድገትይበልጥ አስተዋጽኦ ለማድረግ እንደሚሰሩ ነው የገለጹት።

ግብርን በአግባቡ መክፈል ለመጪው ትውልድ ምቹ የሆነች ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥም የራስን አሻራ ለማኖር የማያስችል ነው ብለዋል።

በከተማው በሆቴል ስራ የተሰማሩት አቶ ሃይሉ ካሳ እና ወይዘሮ ዩስራ መሀመድ በበኩላቸው፤ ግብር መክፈል ለሀገር ልማትና እድገት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ በመገንዘብ የዜግነት ግዴታችን በመወጣት ላይ ነን ብለዋል።

በተለይም'' በአሁኑ ወቅት በሚካሔዱ የልማት ስራዎች ተጠቃሚ በመሆናችን በወቅቱ በተገቢው መንገድ ወደንና ፈቅደን በሚፈለገው መንገድ ግብራችንን መክፈልን እንቀጥላለን'' ነው ያሉት።

በክልሉ መንግስት የተሰጣቸው እውቅናም ይበልጥ ለመስራትና ለሌሎች አርአያ ለመሆን እንዳነሳሳቸው አመልክተዋል፡፡


የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ያሲን አብዱላሂ እንደገለጹት፤ በክልሉ በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የታክስ ተገዢነትን በማሳደግ የክልሉን የልማት ወጪ በራስ ገቢ ለመሸፈን በማቀድ ወደ ስራ ተገብቷል።

በተለይ የታክስ ህጎችን ወደ ስራ በማስገባት ፍትሃዊ የግብር ክፍያዎች እየተፈጸሙ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና ለውጥ እየተመዘገበበት እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በዘንድሮ በጀት ዓመት በክልሉ ከተለያዩ የገቢ ርዕሶች ከ6 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን አመልክተዋል።

በቀጣይም የታክስ አሰባሰብ ስርዓቱን የማዘመን እና የንግዱ ማሕበረሰብ በታክስ አሰባሰቡ ሒደት ላይ ግንዛቤውን የማስፋት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የአፍሪካ የልማትና ትብብር ዓርማ - ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በታዋቂው ታይም መጽሔት ገጽ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...

Sep 14, 2026

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026