የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በዲጅታሉ ዓለም ተወዳዳሪና ስራ ፈጣሪ ዜጎችን ለማፍራት አስችሏል

Jul 30, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ) ፡- የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ተወዳዳሪና ስራ ፈጣሪ ዜጎች ለማፍራት እያስቻለ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ገለፀ።

የቢሮ ኃላፊው አቶ ሰላሙ አማዶ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በክልሉ በዲጅታል ቴክኖሎጂ ተወዳዳሪና ስራ ፈጣሪ ዜጎችን በማፍራት ረገድ ተጨባጭ ዉጤት እየተመዘገበበት ነው።

በጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ234 ሺህ የሚጠጉ ዜጎች ስልጠናውን የተከታተሉ መሆኑን ነው ያመለከቱት።

ስልጠናውን ከወሰዱት ዜጎች መካከል 185 ሺህ 8 መቶ በላይ የሚሆኑት የእውቅና ሰርተፍኬት አግኝተው የኦን ላይን ስራዎች ላይ በመሳተፍ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ እንዳገኙም ገልፀዋል።

ቢሮው በዲጅታል ቴክኖሎጂው በቂ እውቀት ፣ ክህሎትና እውቅና ያገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ አማራጮችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል።


በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የኮምፒውተር ሳይንስ መምህርት ፀጋነሽ ሞገስ በበኩላቸው ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በዘርፉ የበረኝን እውቅት በማሻሻል በአለማቀፍ ደረጃ ተወዳደሪ ለመሆን አስችሎኛል ነው ያሉት።

ስልጠናውን አጠናቀው ባገኙት የእዉቅና ሰርተፍኬት ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኝላቸው ስራን ለመስራት እንደቻሉ ነው የተናገሩት።


በሆሳዕና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የኮምፒውተር ሳይንስ መምህርት ተስፋ በቀለ በበኩሏ፤ የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ እዉቀትንና ክህሎትን ማሳደጋቸው ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነትን ጨምሮልኛል ነው የሚሉት።

የአትዮ ኮደርስ ስልጠናም በዘርፉ የነበረኝን እውቀት እንዳሻሽልና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ በመሆን ተጠቃሚነቴን ለማሳደግ አስችሎኛል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የአፍሪካ የልማትና ትብብር ዓርማ - ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በታዋቂው ታይም መጽሔት ገጽ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...

Sep 14, 2026

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026