የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ንግድ ትስስርና ዕድገት ቁልፍ ሀገር ነች

Aug 3, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 25/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በቀጣናዊ እና አህጉራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲሁም በንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ወሳኝ ሚና እየተጫወተች የምትገኝ ቁልፍ ሀገር መሆኗን በአፍሪካ የንግድና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራው 'ትሬድ ካታሊስት አፍሪካ' ገለጸ።

ኢትዮጵያ ያሏት የታሪክ፣ የስነ-ህዝብ፣ የመሰረተ ልማት እና የጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ፀጋዎች በቀጣናው ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለማፋጠን ወሳኝ ድርሻ እንድትጫወት አስችለዋታል፡፡



‎እንዲሁም የሃይል እና ትራንስፖርት መረቦችን ለመዘርጋትና በአህጉር ደረጃ የፖሊሲ እና የዲፕሎማሲ አቅጣጫዎችን ለመቀየስ የሚያስችላትን የጎላ ድርሻ ይሰጣታል።

የ'ትሬድ ካታሊስት አፍሪካ' ዋና ሥራ አስፈጻሚ አደሬ አዳንኮ ኒያንጎ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኢትዮጵያ ሰፊ የሕዝብ ቁጥር፣ ትልቅ ኢኮኖሚና በርካታ አምራች ወጣቶች ያላት ሀገር መሆኗን ገልጸዋል።



‎ይህ መልካም አጋጣሚ ሀገሪቱ ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንድታበረክትና ተጽዕኖዋን እንድታሰፋ የሚያስችላት መሆኑንም አስታውቀዋል።


በሀገሪቱ ውስጥ በርካታ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ዘርፎች ለልማትና ለስኬት ሰፊ እድል ይዘው እንደሚገኙ ጠቅሰው፤ በተለይም በግብርና እና በግብርና ማቀነባበር መስኮች ላይ ያሉ ሰፊ ዕድሎችን አንስተዋል፡፡

እንዲሁም እንደ ጤና፣ ትምህርት እና የፋይናንስ አገልግሎቶች ባሉ ቁልፍ ዘርፎችም ትልቅ የእድገት አቅም መኖሩን ጨምረው አብራርተዋል።


በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት እየተሰጣቸው ያሉት ወሳኝ ማዕድናት የኢትዮጵያን ሀገራዊ ብልጽግና በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም እንደሚያስችሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በቀጣናዊ እና አህጉራዊ የኢኮኖሚ እድገት እንዲሁም በንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ወሳኝ ሚና እየተጫወተች የምትገኝ ቁልፍ ሀገር ናት ብለዋል።

በዩናይትድ ኪንግደም በሚገኘው ዓለም አቀፍ ገለልተኛ የፖሊሲ እና ጥናት ተቋም (ODI) ዋና ተመራማሪ ማክሲምን ዲባራ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉር በፍጥነት እያደጉ ካሉ የኢኮኖሚ ማዕከላት አንዷ መሆኗን ገልጸዋል።


ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት እያሰመዘገበች እንደምትገኝ አንስተው፤ በተለይም በግብርና እና በአምራች ዘርፎች የሚታየው የእድገት እንቅስቃሴ ከፍተኛ መሆኑን አስታውቀዋል

ይህ እድገት ኢትዮጵያ የባህረ ሰላጤው ሀገራት ከቀሪው የአፍሪካ አህጉር ጋር የሚኖራቸውን የኢኮኖሚ ትስስር የሚያሳልጥ ስትራቴጂካዊ መድረክ እንድትሆን እንደሚያስችላት ገልጸዋል።



እየተከናወኑ ያሉ የኢንዱስትሪና የግብርና ልማት ሥራዎችም ለሀገራቱ የምግብ ዋስትና እና የኢንቨስትመንት ፍላጎቶች ተስማሚ ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።



‎ተመራማሪው ይህም ኢትዮጵያን አጠቃላይ አህጉራዊውን የንግድና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የሚያስተስስር ቁልፍ ማዕከል እንደሚያደርጋት አስታውቀዋል።


የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026

በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ ናቸው 

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...

Aug 7, 2026