የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

በክልሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን የማስፋት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል

Aug 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባምባሲ፤ ሐምሌ 28/2018 (ኢዜአ)፦በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን የማስፋት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ በክልሉ ሶስተኛውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በባምባሲ ከተማ መርቀው ስራ አስጀምረዋል።


ርዕሰ መስተደድሩ በወቅቱ እንደገለፁት፤ ማዕከሉ የተለያዩ የመንግሥትና የልማት አገልግሎቶችን በአንድ ስፍራ በማቀናጀት የተገልጋዩን እንግልት፣ ጊዜና አላስፈላጊ ወጪ የሚቀንስ ነው።

ማዕከሉ የመንግስትን አሰራር ዘመናዊና ቀልጣፋ በማድረግ ትልቅ ሚና የሚጫወት ሲሆን፤ ይህም ሌብነትና ብልሹ አሠራርን በመከላከል ግልጽ እና ፍትሐዊ አሰራርን ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።

ማዕከሉ ከከተማዋ ዕድገት ጋር የተመጣጠነ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በዘመናዊ እና በተቀላጠፈ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያግዝም ገልጸዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታሁን አብዲሳ በበኩላቸው፥ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የዜጎችን የአገልግሎት እርካታ ያሳደገ እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን የመለሰ ኢንሼቲቭ መሆኑን ተናግረዋል።


በክልሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በማስፋት በተቋማት የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው፤ በቅርቡ በግልገል በለስ እና ከማሺ ከተሞች ተመሳሳይ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ስራ እንደሚጀምር አስታውቀዋል።

የባምባሲ መሶብ የአንድ ማዕከል አራት የከተማ አስተዳደር ሴክተሮችን እንዲሁም ሶስት የፌደራል ተቋማትን ጨምሮ 36 አገልግሎቶችን በአንድ ላይ መስጠት የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አስካለች አልቦሮ፣ በብልፅግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር እንዲሁም የባምባሲ ከተማ አመራሮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026

በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ ናቸው 

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...

Aug 7, 2026