🔇Unmute
ሐረማያ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፡-መንግስት ሌብነትን ለማስቀረት የጀመረውን እርምጃ ከማጠናከር ባለፈ ተግባሩን የሚጸየፍ ትውልድ መገንባት ላይ ይበልጥ መስራት እንዳለበት የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ።
መንግስት የተደራጀ ሌብነት እና ህገ ወጥነትን ለመቅረፍ እየወሰደ ያለውን እርምጃ ከግብ እንዲደርስ ህብረተሰቡ ድርሻውን እንዲወጣም ምሁራኑ መክረዋል።
መንግሥት የተደራጀ ሙስናና ሕገወጥ አሰራርን ለመከላከል በተደራጀ አግባብ ባከናወናቸው ሥራዎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ማስታወቁ ይታወሳል።
በንግድ ዘርፉ የኮንትሮባንድ ንግድ በመፈጸም፣ መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችን አከማችተው አላግባብ የዋጋ ጭማሪ በፈጠሩና የዋጋ ንረት እንዲባባስ ባደረጉ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ መወሰዱም እንዲሁ።
በዚህ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን እንዳሉት፤ መንግሥት የተደራጀ ሌብነትና ሕገወጥ አሰራርን ለመቆጣጠር በቅንጅት እየወሰደ ያለውን እርምጃ ከማጠናከር ባለፈ ተግባሩን የሚጸየፍ ትውልድ መገንባት ላይ ይበልጥ አተኩሮ መስራት አለበት።
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ትምህርትና ስነ ባህሪ ኮሌጅ መምህር ጉያሳ ደሳለኝ (ዶ/ር) እንዳሉት ህገ ወጥነትና ሌብነት የአገርን እድገት የሚጎትቱና የትውልድንም ተስፋ የሚያጨልሙ ናቸው።
መንግስት መረጃና ማስረጃን መሰረት በማድረግ ችግሩን ለማስቀረት መውሰድ የጀመረው እርምጃ አበረታች መሆኑንም ተናግረዋል።
ሌብነት የወጣቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት በመጉዳት ለሀገር እድገት እንቅፋት በመሆኑ እርምጃው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ጉያሳ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
ህገ ወጥነትና ሌብነትን በዘላቂነት ለመከላከል በትውልድ ግንባታ ላይ መስራት እንደሚገባና ለእዚህም የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ መጠናክር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
በተለይ የትምህርት ተቋማት፣ የሃይማኖት ተቋማትና ህብረተሰቡ ጭምር ሌብነትን የሚጸየፍ ትውልድ በማፍራት ረገድ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡
ህገ ወጥነትና የሌብነት ወንጀልን በመከላከል ረገድ የዜጎች ተሳትፎ ወሳኝ ነው ያሉት ደግሞ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት አመራርና ፖሊሲ ጥናት መምህር ሙሉጌታ ገለታ (ዶ/ር) ናቸው።
ተግባሩ ዜጎች የሚያገኙትን የመንግስት አገልግሎት በማስተጓጎል ለመልካም አስተዳደር ችግር መንስኤ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት መንግስት ችግሩን ለመፍታት የተጀመረውን ጥረት እስከ ታችኛው እርከን ማውረድ አለበት ብለዋል።
በዚህ ረገድ ተዋናይ የሆኑ አጥፊዎችን ተጠያቂ ለማድረግ የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ ካስቀጠለ የአገረ መንግስት ግንባታው ቀልጣፋና ውጤታማ እንደሚሆንም አክለዋል።
ሌብነትንና ህገ ወጥነትን የማስቀረት ሥራው ዘላቂ እንዲሆንም መንግስት የጀመረውን የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትና ዲጂታል አሰራርን ተደራሽነት ማስፋፋት እንዳለበትም መምህሩ አንስተዋል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026