🔇Unmute
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 12/2018 (ኢዜአ)፦ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዩናይትድ ኪንግደም የድርድር ቡድን ጋር የሚያካሂደው የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድር በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በመክፈቻው ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ፤ ከ23 ዓመታት በላይ የወሰደውን የኢትዮጵያን የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር በ2026 መጨረሻ ለማጠናቀቅ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ለዩናይትድ ኪንግደም የድርድር ኮሚቴ አባላት አብራርተዋል።

ሚኒስትሩ በንግግራቸው ኢትዮጵያ የልማት ፍላጎቷን ያገናዘበ ገንቢና መፍትሔ-ተኮር የገበያ ሁኔታ ማቅረቧን እና እስከ አሁን ከ11 ሀገራት ጋር ድርድር ማጠናቀቋን አረጋግጠዋል።
የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ለኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት ለሚያደርገው ድጋፍና አጋርነት ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ውይይት ስምምነቱን በይፋ ለመፈራረም የሚያስችል ውጤት እንደሚጠበቅም ተገልጿል።
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...
Aug 7, 2026