የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

በ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ -ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Aug 26, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

በ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 32 ነጥብ 3 በመቶ ተማሪዎችን በማሳለፍ 1ኛ ደረጃን መያዙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤የዛሬ 12 ዓመት ያቋቋምነው የኦሮሚያ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ዘንድሮም ያስፈተናቸውን ተማሪዎች 100% ማሳለፍ ችሏል።

ተማሪ ጃለላ ግርማ ኩሳ 591.6 ወጤት በማምጣት እንደ ሀገር ከፍተኛ ነጥብ በማስመዝገብ አንደኛ ወጥቷል።

በከተማ አስተዳደሩም የእቴጌ መነን የሴቶችና ገላን የወንድ ተማሪዎች አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ 24 ትምህርት ቤቶች ያስፈተናቸውን ተማሪዎች 100 ፐርሰንት ማሳለፍ ችለዋል ብለዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በማህበራዊ ሳይንስ ከሴት ተማሪዎች መካከል ከፍተኛው ውጤት 569.1 ያመጣችዉ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኘው ከቦሌ ሱፕር ሆሊ ሴቪየር ት/ቤት ተማሪ መቅደላዊት ሱራፌል ማሞ መሆኗንም ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቀጣይ ከዚህ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የተጀመረውን ስትራቴጂ በአግባቡ መተግበር፣ የትምህርት አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት፣ ወላጆች ለተማሪዎች ውጤት መሻሻልና ለትምህርት ልማት ስራው ስኬት ባለቤት ሆኖ መስራትና ተማሪዎች ለላቀ ውጤት መትጋት ይጠበቅባቸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡ ግቦች መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው-ዋምኬሌ ሜኔ

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...

Sep 4, 2026

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን ተችሏል

አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...

Aug 17, 2026

በአዳማ ከተማ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር ተሸፍኗል

አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...

Aug 11, 2026

በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ ናቸው 

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦በባሕር ዳር ከተማ የተከናወኑ አበረታች የልማት እንቅስቃሴዎች የብልፅግና አቅጣጫዎችን በግልጽ ያመላከቱ መሆናቸውን ...

Aug 7, 2026