🔇Unmute
ድሬዳዋ፤ መስከረም 3/2019 (ኢዜአ)፡- በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የሌማት ትሩፋት መርሃግብር ኑሯቸውን ማሻሻሉን ተጠቃሚዎች ገለጹ።
በመርሃግብሩ የተገኙ ውጤቶችን በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለጸው ደግሞ የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና ፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ነው።
የሌማት ትሩፋት መርሃግብር ተጠቃሚ የሆኑት አቶ በቀለ ኑረሳ ለኢዜአ እንደገለፁት ፤ ቢሮው የተሻለ የወተት ምርት የሚሰጡ ላሞችን ስላቀረበላቸው ወተት ወደ ገበያ በማቅረብ የተሻለ ገቢ እያገኙ ነው።

ለአካባቢው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራቱን የጠበቀ ወተት በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው፤ ከወተት ምርት ያገኙትን ሀብት ተጨማሪ የወተት ላሞችን ለመግዛት እየተጠቀሙበት መሆኑን አቶ በቀለ ተናግረዋል።
በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ከተካተቱ ወዲህ ኑሯቸውን እየቀየሩ መምጣታቻውን ገልጸዋል።
ከንብ ማነብ ስራ ባገኙት ጥቅም ስራውን ይበልጥ እንዲገፉበት እንዳደረጋቸው የገለፁት ደግሞ ሌላው የሌማት ትሩፋት ኢንሼቲቭ ተጠቃሚ አቶ አብዱልቃድር ሁሴን ናቸው።

ባለፈው ግንቦትና ሰኔ ወራት ብቻ ከ400 ኪሎ ግራም በላይ የማር ምርት ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።
ስራው ጥንቃቄ እና እንክብካቤ እንደሚፈልግ የገለፁት አቶ አብዱልቃድር፤ ከግብርና ባለሙያዎች ጋር በትስስር መስራታቸው ይበልጥ ለማስፋፋት እንዳገዛቸው ተናግረዋል ።
ስራው ወደ ሌሎች አርሶአደሮች መንደር እንዲስፋፋ ከግብርና ቢሮ ጋር ተቀናጅተው እየተንቀሳቀሱ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የግብርና ቢሮ ምርጥ የዕንቁላል ዶሮዎች እና የእርባታ ስፍራ በማመቻቸቱ ወደ ስራ በመግባት ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት እንዳስቻላቸው የተናገሩት ደግሞ በገንደሳር ገጠር ቀበሌ በእንቁላል ማምረት ስራ የተሰማሩ ወይዘሮ አያን መሐመድ ናቸው።
የማህበሩ አባላት ዶሮዎቹን በአግባቡ በመንከባከብ የሚያመርቱትን እንቁላል በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ እያቀረቡ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
የድሬደዋ አስተዳደር ግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ሚስራ አብደላ የሌማት ትሩፋት መርሃግብር ገጠሩን ህብረተሰብ የእንሰሳት ሃብቱን በአግባቡ ተጠቅሞ ኑሮውንና ህይወቱን እንዲለውጥ እያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል ።

በዚህም በርካታ የገጠርና የከተማ ቤተሰቦች ተገቢውን ስልጠና፣ ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ የማር፣ የዶሮ ፣ የእንቁላል እና የወተት ምርቶች በስፋት ማምረት መቻላቸውን ገልፀዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026