የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

መንግስት ለማዕድን ዘርፍ በሰጠው ትኩረት በድንጋይ ከሰል ዘርፍ ውጤታማ ሥራ እንድናከናውን ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮልናል

Sep 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ መስከረም 11/2019 (ኢዜአ)፦መንግስት ለማዕድን ዘርፍ በሰጠው ትኩረትና ድጋፍ በድንጋይ ከሰል ዘርፍ ውጤታማ ሥራ እንዲያከናውን ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረለት ዮ ሆልዲንግ ንግድና ማኑፋክቸሪንግ የተሰኘ ሀገር በቀል ኩባንያ አስታወቀ።

የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እና የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ቦረዳ ወረዳ የሚገኘውን ዮ ሆልዲንግ የድንጋይ ከሰል ማምረቻና ማጠቢያ ፋብሪካ የሥራ እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል።

ዮ ሆልዲንግ የድንጋይ ከሰል ማምረቻና ማጠቢያ ፋብሪካ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መኳንንት አለሙ እንደገለጹት፤ ኩባንያው በቤንሻንጉል ጉሙዝ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች 2 የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካዎችን ገንብቶ እየሠራ ይገኛል።


‎የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካዎቹ በሰዓት 400 ቶን የታጠበ የድንጋይ ከሰል በማምረት የሀገሪቱን ትላልቅ ኩባንያዎች የግብዓት አቅርቦት ችግር እየፈቱ ይገኛሉ ብለዋል።

‎ኩባንያው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ቦረዳ ወረዳ በሚገኘው ዮ ሆልዲንግ የድንጋይ ከሰል ማምረቻና ማጠቢያ ፋብሪካው ብቻ በአዲሱ በጀት ዓመት በሁለት ወራት ውስጥ ከ2 መቶ ሺህ ቶን በላይ የድንጋይ ከሰል በማጠብ ለገበያ ለማቅረብ ዝግጁ ማድረጉን አስታውቀዋል።

‎በዚህም ፋብሪካዎቹ የድንጋይ ከሰል ሀብትን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማበልጸግ ለሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች አስተማማኝ የኃይል ግብዓት እያቀረቡ ይገኛሉ ብለዋል።

‎‎ዮ ሆልዲንግ በያዝነው ዓመት በሁለት የተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ሁለት ግዙፍ የከሰል ማጠቢያ ፋብሪካዎችን ለመገንባት በዝግጅት ላይ የሚገኝ መሆኑን አስታውቀዋል።


‎የሀገር ውስጥ የምርት ፍላጎትን ሙሉ በሙሉ በመቅረፍ ወደ ውጭ ሀገራት ምርቱን ኤክስፖርት ለማድረግ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

‎ኩባንያው የሚያመርተው ከፍተኛ ጥራት ያለው የታጠበ የከሰል ምርት የፋብሪካዎችን የኃይል ፍላጎት በማሻሻል የነዳጅ ፍጆታን እና የምርት ወጪን እየቀነሰ እንደሆነ አመልክተዋል።

‎ኢትዮጵያ በየዓመቱ ለድንጋይ ከሰል ግዥ የምታወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ለማስቀረት ኩባንያው ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አስታውቀዋል።

‎ይህም የሀገሪቱን የኢንዱስትሪ ልማት፣ የኢኮኖሚ ዕድገት እና የውጭ ምንዛሬ ግኝት በማሳደግ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።

‎መንግስት ለማዕድን ዘርፍ የሰጠው ትኩረትና ድጋፍ በድንጋይ ከሰል ዘርፍ ውጤታማ ሥራ እንዲያከናውን ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረለት ዋና ስራ አስፈጻሚው አስታውቀዋል።

‎የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ ኤፍሬም ታደሰ በበኩላቸው፤ ፋብሪካው ለበርካታ ወገኖች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እየፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች ላይ በመሳተፍም የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የክልሉ ከተሞችን ለኑሮ ምቹና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል

ቦንጋ ፣ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከተሞችን ለኑሮ ምቹ፣ ለንግድና ኢንቨስትመንት ተመራጭ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እን...

Oct 29, 2026

የግብርና ልማት ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል

ዱራሜ ፤ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ አሰራርና የተቀናጀ የግብርና ልማት ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥና...

Oct 21, 2026

ኢትዮጵያ እና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በንግድና ኢንቨስትመንት ያላቸው ግንኙነት እያደገ ነው

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በንግድና ኢንቨስትመንት መስክ ያላቸው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን...

Oct 21, 2026

የመደመር መንግስት ለሕዝብ የገባው ቃል ስኬታማ እንዲሆን የድርሻችንን እንወጣለን

ባህር ዳር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግስት በህዝብ ተሳትፎ ስኬታማ ለማድረግ የሚያከናውናቸውን ተግባራት እንደግፋለን ሲሉ የባህር ዳር ከተማ...

Oct 9, 2026