🔇Unmute
በኢትዮጵያ አሁን ላይ በተለያዩ መስኮች እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች የሚጨበጡ ስኬቶችን እያመጡ ነው።
ከነዚህ ስራዎች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው የሀገሪቱን ከተሞች ገጽታና የነዋሪዎቿን የኑሮ ዘይቤ በከፍተኛ ደረጃ እየቀየረ ያለው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ነው።
ይህ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት፣ በዋና ዋና ከተሞች የሚከናወኑት የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ነባር መጨናነቆችን፣ የመሠረተ ልማት እጥረቶችንና የከተማ አስተዳደር ጉድለቶችን በመቅረፍ ከተሞችን ዘመናዊ፣ ጽዱ እና ለኑሮ ተስማሚ አድርገዋቸዋል።
በአጭር ጊዜ ውስጥ ያስመዘገበው ስኬትና የፈጠረው አርአያነት አሁን ላይ አዲስ አበባን አልፎ በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች ወደ ሚገኙ ከ75 በላይ ከተሞች ተዳርሷል።
በኮሪደር ልማቱ አማካኝነት የከተሞች ገጽታ በመሠረታዊነት ተቀይሯል። ቀደም ሲል ለዕግረኛ እና ለአካል ጉዳተኞች ፈታኝና አዳጋች የነበሩ መንገዶች ዛሬ ሰፊና ጥራት ባላቸው የኮንክሪት ንጣፎችና የብስክሌት መስመሮች ተቀይረዋል።

በከተሞች የሚገኙ የመዝናኛ ፓርኮች፣ የማረፊያ ስፍራዎች እንዲሁም ንጹህና ደረጃቸውን የጠበቁ ቦታዎች የዜጎችን ማኅበራዊና ሰብአዊ ክብር ከፍ ያደረጉ ሲሆን፣ እነዚህ ጥራት ያላቸው መሠረተ-ልማቶች የነገውን ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር የተጣሉ ጠንካራ መሠረቶች ናቸው።
ይህም የከተሞችን ውበትና ደረጃ ከማሳደግ ባሻገር ለንግድ፣ ለቱሪዝም እና ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል።
በዘመናዊ የጎዳና ላይ መብራቶችና የደህንነት ካሜራዎች የታገዙ ከተሞች በቀን ብቻ ሳይሆን በሌሊትም የንግድና የኢኮኖሚ ማዕከል እንዲሆኑ በር በመክፈታቸው የ24 ሰዓት የስራ ባህልን በመፍጠር ለአያሌ ወጣቶችና ለነጋዴዎች አዲስ የሥራ ዕድል ፈጥሯል።
በሌላ በኩል፣ ይህ ስትራቴጂካዊ ልማት ኢትዮጵያን ወደ ቋሚ የኮንፈረንስ፣ የንግድ እና የባህል ቱሪዝም መዳረሻነት እየቀየራት ይገኛል።
በተለይም የከተሞችን ማህበራዊ መስተጋብርና የሕዝብ አንድነትን በማጠናከር ረገድ የኮሪደር ልማቱ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ የላቀ ነው።
በኮሪደሩ በተለያየ እድሜ ክልል እና ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ዜጎች የሚገናኙበት ምቹ ዕድል መፈጠሩ፣ የዕለት ተዕለት መስተጋብራቸውን በማጠናከር በሕዝቦች መካከል ያለውን አብሮነትና ማህበራዊ ትስስር ይበልጥ ያጠናክራል።
የነገዋ ኢትዮጵያ በዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅም ያደገችና አሰራሯ የዘመነ መሆኑን የሚያረጋግጥ ተግባራዊ እርምጃ በኮሪደሮቹ ውስጥ መዘርጋት ጀምሯል።

ስራው ከቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር በቅንጅት በማከናወን ዘመናዊ የትራፊክ ቁጥጥር ሥርዓቶች እና የስማርት ከተማ (Smart City) መተግበሪያዎች መሰረተ ልማት አብሮ እየተዘረጋ ይገኛል።
በተጨማሪም በኮሪደሮቹ ውስጥ እየተከናወነ ያለው መጠነ ሰፊ የዛፍ ተከላ እና የወንዞች ዳርቻ ልማት ከተሞች ከአየር ንብረት ለውጥ ስጋትና ከሙቀት በመከላከል፣ ትውልዱ ንጹህና ጽዱ ስፍራን በመረከብ ጤናማ ማህበረሰብ ለመገንባት ያስችላል።
በአጠቃላይ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ከአንድ ከተማ ገጽታ ማሻሻል ባሻገር፣ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ በርካታ ክልል ከተሞች ላይ በመስፋፋት ሀገራዊ ለውጥ እየፈጠረ ይገኛል።
የዚህ ዘርፈ ብዙ ልማት ፍሬ ዛሬ ላይ የኑሮ ዘይቤን እያሻሻለ እንደሚገኘው ሁሉ፣ ለወደፊቱ ትውልድም የኩራት ምንጭ የሆነ ዘላቂ ሀብት ሆኖ ይሸጋገራል፤ ዛሬ የሚሰራው ስራ ለነገው ትውልድ የሚተርፍ ተምሳሌታዊ ተግባር ነው።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026