🔇Unmute
ጋምቤላ ፤መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል የመንግሥትና የሕዝብ ሀብትን ከብክነት ለመታደግ የሚያስችሉ የክዋኔ ኦዲት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አስታወቀ።
በክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ለፋይናንስ የክዋኔ ኦዲት ዳይሬክተሮችና ሌሎች ከፍተኛ ባለሙያዎች የተዘጋጀው የአቅም ግንባታ ስልጠና ዛሬ ተሰጥቷል።
በወቅቱም በመሥሪያ ቤቱ ዋና ጄኔራል ኦዲተር አቶ ኡጁሉ ኡጁሉ እንደገለጹት፤ በክልሉ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብትን ከብክነት ለመታደግ የሚያስችሉ የክዋኔ ኦዲት ስራዎች ይጠናከራሉ።

መሥሪያ ቤቱ ባለፈው በጀት ዓመት ባከናወናቸው የፋይናንስና የክዋኔ ኦዲት ሥራዎች በርካታ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብትን ከብክነት ለመታደግ መቻሉን ተናግረዋል።
ባለፈው የበጀት ዓመት በተከናወኑ የሒሳብ ምርመራ ሥራዎች ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ማስመለስ እንደተቻለ ገልጸዋል።
በተያዘው በጀት ዓመትም ባለፈው ዓመት የተጀመሩትን ሥራዎች ይበልጥ በማጠናከር የሕዝብና የመንግሥትን ሀብትን ከብክነት በመጠበቅ ለታለመላቸው የልማት ሥራዎች እንዲውሉ በትኩረት እንደሚሰራም አስታውቀዋል።
በዘንድሮው በጀት ዓመት በ78 የክልል፣ የዞንና የወረዳ መሥሪያ ቤቶች ላይ የፋይናንስና የክዋኔ ኦዲት ሥራዎችን ለማከናወን ዕቅድ ተይዞ ወደ ትግበራ መገባቱን ተናግረዋል።
የስልጠናው ዓላማም መሥሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ ያቀዳቸውን ሥራዎች ለማሳካትና የዘርፉ ባለሙያዎችን የሥነ-ምግባር ክህሎት ለማዳበር ያለመ መሆኑንም አክለዋል።
ዱራሜ ፤ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ አሰራርና የተቀናጀ የግብርና ልማት ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥና...
Oct 21, 2026
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በንግድና ኢንቨስትመንት መስክ ያላቸው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን...
Oct 21, 2026
ባህር ዳር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግስት በህዝብ ተሳትፎ ስኬታማ ለማድረግ የሚያከናውናቸውን ተግባራት እንደግፋለን ሲሉ የባህር ዳር ከተማ...
Oct 9, 2026
አዳማ ፤መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦ በኦሮሚያ ክልል የኢንቨስትመንት ሕጎችና አሠራሮች መሻሻላቸው እንዲሁም አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ እንዲደገፉ መደረጉ ክልሉ...
Oct 4, 2026