🔇Unmute
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም የዕዳ ጫናን በመቀነስና የዋጋ ንረትን በማረጋጋት ረገድ ውጤት ማስመዝገቡን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ገለጹ፡፡
ሁለተኛው ፋይናንስ ፎረም 2026 በዐድዋ ድል መታሰቢያ መካሄድ ጀምሯል፡፡
የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ስኬታማነት ለኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ እና ታላቅ ርዕይ እንደ ትልቅ ማሳያነት የሚጠቀስ ነው፡፡
በዚሁ ወቅት በተካሄደ የፓናል ውይይት የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እየተገበረች ትገኛለች።
የዕዳ ማሻሻያ ስምምነት በውጤታማነት መጠናቀቁን አመልክተው፤ የዕዳ ማሻሻያው ከሰፊው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ጋር ተያይዞ የፊስካልና የውጭ ምንዛሬ ጫናን ለመቀነስ ዕድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡
የውስጥ ገቢ አሰባሰብ፣ የባንክ ቁጠባ፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት፣ የመንግስትና የግል አጋርነት፣ የዲያስፖራ ፋይናንስና የካፒታል ገበያ ልማት የሀገሪቷን ዘላቂ የፋይናንስ አቅም እንደሚያጠናክሩም አስረድተዋል።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ የዋጋ ንረትን በመቆጣጠር ረገድ ውጤት ማስመዝገቡን ገልጸዋል።

ከሪፎርሙ አንድ ዓመት በፊት ከ26 በመቶ በላይ የነበረው ዓመታዊ አማካይ የዋጋ ንረት ከሪፎርሙ ከአንድ ዓመት በኋላ ከ16 በመቶ በላይ ወደሆነ ደረጃ ዝቅ ማለቱን ገልፀዋል።
ይህ ውጤት የተገኘው በቅንጅት በተከናወኑ የገንዘብና የፊስካል ፖሊሲ ሪፎርሞች መሆኑን ገልጸዋል።
የብሔራዊ ባንክ የብድር ዕድገት ጣሪያ፣ ቀጥተኛ የፊስካል ማስተካከያ ፋይናንስን ማቆምና የፊስካል ማጠናከር በፍላጎት በኩል የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የተወሰዱ ዋና እርምጃዎች መሆናቸውን አስረድተዋል።
በአቅርቦት ረገድ የመስኖ፣ የሜካናይዜሽን፣ የመሬት አጠቃቀምና የክላስተር እርሻ ስራዎች የምርትና የምርታማነት ዕድገትን በማሳደግ የምግብ አቅርቦትን ማሻሻላቸውን ጠቁመዋል።
በተለይም የብሔራዊ የስንዴ ፕሮግራም ኢትዮጵያን ከስንዴ አስመጪነት ራሷን ወደ መቻል እንዳሸጋገራት ገልጸዋል።
ሆኖም የዋጋ ንረትን በዘላቂነት ለመቆጣጠር የውጭና የውስጥ ስጋቶች እንዳሉ ጠቁመው፤ የአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል፣ የነዳጅና የመጓጓዣ ዋጋ ጭማሪ፣ የገንዘብ ፖሊሲ ተአማኒነትና ዘላቂ የፊስካል ማጠናከር ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውን አስረድተዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከኃይል ማመንጫነት በላይ ትርጉም ያለው፣ የአፍሪካን የውስጥ...
Sep 14, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ውህደትን ማፋጠን ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ እና ለተቀመጡት ግቦች መሳካት ጉል...
Sep 4, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የመንግስትና የህዝብ ሀብትን ከብክነት ማዳን መቻሉን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ...
Aug 17, 2026
አዳማ፤ ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፡-በአዳማ ከተማ ከልማት ሥራዎች ጎን ለጎን ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን መሬት ታርሶ በዘር መሸፈኑን የከተማዋ ግብርና ጽሕ...
Aug 11, 2026