የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ የማር ምርትን በእጥፍ ለማሳደግ ዘመናዊ የንብ ቀፎ እየተሰራጨ ነው

Oct 22, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

መቱ ፤ ጥቅምት 11/2019 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን በተያዘው በጀት ዓመት የማር ምርትን በእጥፍ ለማሳደግ ከ900 ሺህ በላይ ዘመናዊ የንብ ቀፎዎች ለአርሶ አደሮችና ማህበራት እየተሰራጨ ነው።

ኢትዮጵያ በንብ ማነብና በማር ምርት ትልቅ አቅም ካላቸው ሀገራት አንዷ ብትሆንም፣ የአመራረት ዘዴው በብዛት በባህላዊ ቀፎዎች ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ከዘርፉ የሚገኘው ጥቅም ከእቅድ በታች ሆኖ ቆይቷል።

ይህንን ክፍተት ለመድፈንና የአርሶ አደሩን ገቢ ለማሳደግ መንግሥት በሀገር አቀፍና በክልል ደረጃ የጀመረው የማር ኢንሼቲቭ አሰራርን ዘመናዊ በማድረግ ረገድ ትልቅ ንቅናቄ እየተፈጠረ ይገኛል።


ኢንሼቲቩ አርሶ አደሩንና ወጣቶችን በማህበራት በማደራጀት፣ ዘመናዊ የንብ ቀፎዎችንና የሙያ ስልጠናዎችን በማቅረብ እንዲሁም ጥራቱን የጠበቀ የማርና ሰም ምርት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ያለመ ነው።

በተለይም በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኙ ለንብ ማነብ ተስማሚ የሆኑ ተፈጥሮአዊ የደን ሀብቶች፣ ኢንሼቲቩን በስፋት በመተግበር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ለማስገኘት ምቹ ሁኔታ ፈጥረዋል።


የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ፤ ባለፉት አምስት አመታት በዞኑ አንድ ሚሊዮን ዘመናዊ ቀፎዎችን ለአርሶ አደሮችና ለማሕበራት ማሰራጨት መቻሉን ተናግረዋል።

በእነዚህ ዓመታት ከ90 ሺህ ቶን በላይ የማር ምርት መገኘቱን በማንሳት በተያዘው ዓመትም የዘመናዊ ቀፎ አቅርቦት መጠንን በእጥፍ በመጨመር ምርትን ለማሳደግ የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህም የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥን ጨምሮ የማር ምርት በገበያ ያለውን ዋጋ እንደ እድል በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ የሚያግዝ ነው በማለት ተናግረዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዞኑ አሌ ወረዳ በማሕበር ለተደራጁ ወጣቶች ዘመናዊ ቀፎ የተሰጠ ሲሆን በመስኩ ጠንክረው በመስራት ሕይወታቸውን ለመቀየር እንደሚጥሩ ተጠቃሚ ወጣቶች ተናግረዋል።


ወጣት አሰፋ ወንድሙ ከእነዚህ አንዱ ሲሆን በንብ ማነብ ስራው ጠንክሮ በመስራት ሕይወቱን ለመቀየር እንደሚሰራ ተናግሯል።

ዛሬ ያገኙትን ዘመናዊ ቀፎ እንደመነሻ በመጠቀምና አስፋፍተው በመስራት የተሻለ ቦታ ለመድረስ ማለማቸውን የተናገረው ደግሞ ወጣት ሰይድ ኢድሪስ ነው።


ወጣት ቶፊቅ አህመዲን በበኩሉ ከስምንት ወራት በፊት በ120 ዘመናዊ ቀፎዎች የንብ ማነብ ስራ ላይ መሰማራቱን አንስቶ በመንግስት በኩል የቀረበላቸውን ቀፎ በአግባቡ በመጠቀም በዓመቱ እስከ 500 ኪሎ ግራም ማር ለማግኘት ማቀዱን ተናግሯል።

ወደፊት በዚሁ ዘርፍ በስፋት ለመሳተፍና እስከ ኢንቨስተመንት ደረጃ ለማሳደግ አላማ እንዳለውም ወጣቱ ተናግሯል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የግብርና ልማት ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል

ዱራሜ ፤ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ አሰራርና የተቀናጀ የግብርና ልማት ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥና...

Oct 21, 2026

ኢትዮጵያ እና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በንግድና ኢንቨስትመንት ያላቸው ግንኙነት እያደገ ነው

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በንግድና ኢንቨስትመንት መስክ ያላቸው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን...

Oct 21, 2026

የመደመር መንግስት ለሕዝብ የገባው ቃል ስኬታማ እንዲሆን የድርሻችንን እንወጣለን

ባህር ዳር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግስት በህዝብ ተሳትፎ ስኬታማ ለማድረግ የሚያከናውናቸውን ተግባራት እንደግፋለን ሲሉ የባህር ዳር ከተማ...

Oct 9, 2026

በክልሉ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ መመራታቸው የኢንቨስትመንት ሳቢነቱን አሳድጎታል

አዳማ ፤መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦ በኦሮሚያ ክልል የኢንቨስትመንት ሕጎችና አሠራሮች መሻሻላቸው እንዲሁም አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ እንዲደገፉ መደረጉ ክልሉ...

Oct 4, 2026