የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

ሳሞ ኤታ -የየሞች የፈውስ ፍለጋ ዕለት

Oct 28, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

በእንዳልካቸው ደሳለኝ- ኢዜአ ወልቂጤ ቅርንጫፍ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በየም ዞን የሚገኘው የቦር ተራራ ከባሕር ጠለል በላይ በ2939 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝና የበርካታ ዕፅዋት መገኛና በየም ማኅበረሰብ ልዩ ስፍራ የሚሰጠው ነው።

ከቦር ተራራ የሚነፍሰው ንጹሕ አየርና ከዕፅዋቱ የሚገኘው ፈውስ በየም ማኅበረሰብ ዘንድ ለተራራው ትልቅ ክብርን አጎናጽፎታል።

በየዓመቱ ጥቅምት 17 ቀን ላይ የቦር ተራራን ፈውስ ፍለጋ በርካቶች ወደ ስፍራው ያቀናሉ። በትውልድ ቅብብሎሽ ዘመንን እየተሻገረ ዛሬ ላይ እንዲደርስ ያደረገውም ከተራራው የሚገኘው ፈውስ ነው።

"ሳሞ ኤታ" ይሉታል የየም ሰዎች ጥቅምት 17 በቦር ተራራ ተፈጥሮን ማዕከል ባደረገ የአብሮነት፣ የፍቅርና የፈውስ መንፈስ በድምቀት የሚታደሙበትን የመድኃኒት ዕፅዋት ለቀማ ሥነ ሥርዓት።

ይህ ቀን የአባቶች ጥበብ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍበት፣ የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር ያለው ጥልቅ ዝምድና የሚታደስበት ዕለት ነው።

የጥቅምት 17 ጸሐይ ከተራራው አናት ብቅ ስትል በቦር ተራራ ግርጌና ዙሪያ ገብ የጤዛ ጠብታዎች እንደ ዕንቁ ያበራሉ።

አባቶችና እናቶች፣ ወጣቶችና ልጆች በባህላዊ አልባሳት ተውበው ከየአቅጣጫው ወደ ተራራው ይተማሉ፤ የመድኃኒት ዕፅዋትን ለመልቀም።

ለቀማው ከመጀመሩ በፊት አባቶች ፊት ለፊት በመሆን ለሀገር ሰላም፣ ለሕዝብ ጤናና ለምድር በረከት ምስጋና ያቀርባሉ። ይህ የዕለቱ የመጀመሪያው የፍቅር ማሳያ ነው።

ሳሞ ኤታ፣ በመድኃኒት ዕፅዋት አካላዊ ሕመምን ወይም ፈውስን መስጠት ብቻ ሳይሆን፣ አብሮ በመሰብሰብ የሥነ ልቦና እርካታና ማኅበራዊ ትስስርን ያጠናክራል።

የቦር ተራራ ተጠብቆ የሚቆይና በዓመት አንድ ቀን ብቻ የመድኃኒት ዕፅዋት የሚሰበሰብበት፣ ማንም የማይደርስበት በመሆኑ ለለቀማው የተመረጠ መሆኑን በየም ማኅበረሰብ የባህላዊ ዕውቀት አባት የሆኑት አቶ ጌታቸው ኃይለ ማርያም ያስረዳሉ።

ጥቅምት 17 ክረምቱ አልፎ ጥቅምት ሲገባ የተለያዩ ቅጠላ ቅጠሎችን በብዛትና በዓይነት ለማግኘት፣ ብሎም ከሥራሥር እስከ አበባ ድረስ በእሸትነት የሚደርሱበት በመሆኑ ተመራጭ ወቅት አድርጎታል ይላሉ።

በዕለቱ የሚሰበሰበው የዕፅዋት ቅጠል፣ ሥራሥርና አበባ በባህላዊ መንገድ ተቀምሞ ለሰውና ለእንስሳት መድኃኒት ይዘጋጃል።

"ሳሞ ኤታ" ማለት ከራሚ መድኃኒት እንደማለት ሲሆን፣ ተቀምሞ ዓመት የሚቀመጥ፣ ፈዋሽነቱ የጎለበተ ባህላዊ መድኃኒት የሚል ትርጉም እንደሚይዝ የየም አባቶች ይናገራሉ።

በዚህ ቀን የተለቀመው የመድኃኒት ዕፅዋት ከተለቀመበት ቀን እስከሚቀጥለው ዓመት ጥቅምት 17 ድረስ እንደሚያገለግል ያስረዱት ደግሞ ሌላዋ የባህል መድኃኒት አዋቂ ወይዘሮ አስካለ ካሳ ናቸው።


የሞች ከሌሎች የግብርና ሥራዎቻቸው ጎን ለጎን የባህል መድኃኒቶችን በመሸጥ ኑሯቸውን እየመሩ መሆኑንም ያስረዳሉ። በየሞች የሚዘጋጀው ባህላዊ መድኃኒት ጥቅም ላይ የሚውለው ሕመም ሲያጋጥም ብቻ ሳይሆን በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል ጭምር ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ዘሪሁን እሸቱ፣ የየም ማኅበረሰብ መድኃኒት አዋቂ አባቶችና እናቶች ታናናሾቻቸውን አስከትለው ወደ ቦር ተራራ በመውጣት የለቀማ ሂደቱን በሥርዓት ስለሚያካሂዱ፣ ይህ የሀገር በቀል ዕውቀት ሽግግር ማሳያም ነው ይላሉ።


የመድኃኒት ለቀማውን ትዕይንት ለመመልከት የሚመጡ ቱሪስቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ሌላው ትልቁ ትሩፋት ነው ያሉት አቶ ዘሪሁን፣ ለቀማው ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት መሆኑን አስረድተዋል።

ይህም ለአብሮነትና የሀገር በቀል ዕውቀትን ለመቅሰም ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል። እንደነዚህ ያሉ ሀገር በቀል ዕውቀቶችን አልምቶና አዘምኖ ለመጠቀም የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የግብርና ልማት ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል

ዱራሜ ፤ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ አሰራርና የተቀናጀ የግብርና ልማት ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥና...

Oct 21, 2026

ኢትዮጵያ እና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በንግድና ኢንቨስትመንት ያላቸው ግንኙነት እያደገ ነው

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በንግድና ኢንቨስትመንት መስክ ያላቸው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን...

Oct 21, 2026

የመደመር መንግስት ለሕዝብ የገባው ቃል ስኬታማ እንዲሆን የድርሻችንን እንወጣለን

ባህር ዳር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግስት በህዝብ ተሳትፎ ስኬታማ ለማድረግ የሚያከናውናቸውን ተግባራት እንደግፋለን ሲሉ የባህር ዳር ከተማ...

Oct 9, 2026

በክልሉ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ መመራታቸው የኢንቨስትመንት ሳቢነቱን አሳድጎታል

አዳማ ፤መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦ በኦሮሚያ ክልል የኢንቨስትመንት ሕጎችና አሠራሮች መሻሻላቸው እንዲሁም አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ እንዲደገፉ መደረጉ ክልሉ...

Oct 4, 2026