🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17/2019 (ኢዜአ)፦በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የከተሞችን ገጽታ ከመለወጡ ባሻገር አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በመሳብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን እያነቃቃ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ምሁራን ገለጹ።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የኮሪደር ልማት ከተሞችን ለኑሮ ምቹ፣ ንጹህና ስልጡን በማድረግ ትልቅ ምዕራፍ ከፍቷል።
ይህ ልማት በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች በስፋት በመከናወኑ ከተሞችን ሁሉን አቀፍ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሕይወት ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
የኮሪደር ልማት ከከተማ ውበትና ገጽታ ባለፈ የሀገሪቱን የዕድገት አቅጣጫ በከፍተኛ ደረጃ እየቀየረ ያለ እና የነገዋን ሀገር ዛሬ ላይ የመቅረጽ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው።
በከተሞች የሚገኙ የመዝናኛ ፓርኮች፣ የማረፊያ ስፍራዎች እንዲሁም ደረጃቸውን የጠበቁ ቦታዎች የዜጎችን ማኅበራዊና ሰብአዊ ክብር ከፍ ያደረጉ ናቸው።
ኢዜአ ያነጋገራቸው የዘርፉ ምሁራን እንዳሉት፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የከተሞችን ዘመናዊ ገጽታ ከማሳደጉም በላይ የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እያነቃቃ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት የከተማ ልማት እና የመሰረተ ልማት ተመራማሪ ተካልኝ አርፍጮ እንደገለጹት፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለው የኮሪደር ልማት የከተሞችን ገጽታ በመቀየር ለዘመናዊ ከተማ ግንባታ እና ለኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አብራርተዋል።
ተመራማሪው እንዳሉት፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ሃሳብ አመንጪነት የተጀመረው ይህ ሀገራዊ ንቅናቄ አዲስ አበባን ጨምሮ ከ75 በላይ የክልል እና የዞን ከተሞች በስፋት እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል።
በኮሪደር ልማቱ መንገዶች ከመስፋታቸው ባሻገር የአረንጓዴ ልማት፣ የብስክሌት መስመሮች እና የእግረኛ መንገዶች በጥራት መገንባታቸው የዜጎችን እንቅስቃሴ በማሳለጥ በኩል ትልቅ እገዛ ማድረጉን አንስተዋል።
የኮሪደር ልማቱ የመንገድ፣ የአረንጓዴ እና የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን ያካተተ በመሆኑ ከፍተኛ የስራ እድል መፍጠሩን ተመራማሪው አክለው ገልጸዋል።
በተጨማሪም የከተሞች መሰረተ ልማት መሟላት የሀገር ውስጥ እና የውጭ ባለሀብቶች በኢንቨስትመንት ዘርፍ ያላቸውን ተሳትፎ የሚያበረታታ መሆኑን ጥናቶችን ዋቢ በማድረግ ተናግረዋል።

ሌላኛው አስተያየት ሰጪ በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት የከተማ እና መሰረተ ልማት ጥናትና ምርምር ማዕከል ተመራማሪ ይልቃል ታሪኩ በበኩላቸው፤ ባለፉት ዓመታት በስፋት ሲከናወን የቆየው የኮሪደር ልማት የአዲስ አበባንና የክልል ከተሞችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በማሳለጥ ረገድ ትልቅ ሚና መጫወቱን ገልጸዋል።
የኮሪደር ልማቱ የንግድ እንቅስቃሴን፣ የኢንቨስትመንት ፍሰትን እና የሥራ ዕድል ፈጠራን በማነቃቃት ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አብራርተዋል።
ዱራሜ ፤ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ አሰራርና የተቀናጀ የግብርና ልማት ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥና...
Oct 21, 2026
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በንግድና ኢንቨስትመንት መስክ ያላቸው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን...
Oct 21, 2026
ባህር ዳር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግስት በህዝብ ተሳትፎ ስኬታማ ለማድረግ የሚያከናውናቸውን ተግባራት እንደግፋለን ሲሉ የባህር ዳር ከተማ...
Oct 9, 2026
አዳማ ፤መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦ በኦሮሚያ ክልል የኢንቨስትመንት ሕጎችና አሠራሮች መሻሻላቸው እንዲሁም አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ እንዲደገፉ መደረጉ ክልሉ...
Oct 4, 2026