የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

የአፋር ክልል የቱሪዝም ፀጋዎች የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እያሳደጉ ነው

Nov 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 24 /2019 (ኢዜአ)፦ በአፋር ክልል የሚገኙ ተፈጥሯዊና ባህላዊ የቱሪዝም ሀብቶችን በማልማት የህዝቡን ዘላቂ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች አበረታች ውጤት እያስገኙ መሆናቸውን የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ።

የትልቅ ሀገር ትልቅ ሕዝብ እና ታላቅ ርዕይ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ የህዝቦቿን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተጋች ትገኛለች።

በዚህም የቱሪዝም ዘርፍን ለማሳደግና የሀገራችንን ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ ጸጋዎች በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል ባለፉት ጥቂት ዓመታት በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

እነዚህ የተቀናጁ ጥረቶች ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን ግዙፍ አቅም ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ጥቅም በመቀየር የዜጎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ ይገኛሉ።

የአፋር ክልል ቱሪዝም ቢሮ የፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ አብዱ አህመድ ለኢዜአ እንዳሉት፤ መንግሥት የክልሉን የቱሪዝም አቅም ለማሳደግ የመዳረሻና የመሠረተ ልማት ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።


ከዚህም ባለፈ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ በሆቴል፣ በሎጅ፣ በሪዞርትና በተለያዩ የቱሪዝም አገልግሎቶች ላይ እንዲሳተፉ ምቹ የሥራ ከባቢ ተፈጥሯል ብለዋል።

የቱሪዝም ልማት ከመዳረሻዎችና መሠረተ ልማት ግንባታ ባሻገር ማኅበረሰቡን በጽዳት፣ ምግብ አቅርቦት፣ በአስጎብኝነትና በሌሎችም አገልግሎቶች ቀጥተኛ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

የአፋር ህዝብ ሰው አክባሪና እንግዳ ተቀባይ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ የክልሉን ዓመታዊ የጎብኝዎች ቁጥር ከአምስት ሺህ ወደ 40 ሺህ ለማሳደግ ዕቅድ ተይዟል ብለዋል።

ለዚህም በሰመራና በዙሪያዋ ያሉ የቱሪስት መዳረሻዎችን በውሃና ኤሌክትሪክ አቅርቦት፣ በመንገድና መጠለያ አገልግሎቶች ለማስተሳሰር፤ ታሪካዊና ሳይንሳዊ ቅርሶችን በመጠበቅ ለጎብኚዎች ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።


የክልሉ መንግሥት ለኢንቨስትመንት ተስማሚ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በመለየት የመሬት አቀማመጥ፣ የግንባታ ዲዛይንና የኢንቨስትመንት አዋጭነት መረጃዎችን እያዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህም ባለሃብቶች የአፋር ክልል ያለውን እምቅ የቱሪዝም አቅም እንዲረዱ እንደሚያደርግ ገልጸው፤ በኤርታሌ አካባቢ የጎብኝዎችን ቆይታ ለማራዘም ለሎጅ ግንባታ ፈቃድ መሰጠቱንም ገልጸዋል።

በአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ የፓርኩን ጥበቃ ለማጠናከርና በሰውና በዱር እንስሳት መካከል የሚከሰተው መቀራረብ ችግር እንዳይፈጥር አጥር መሰራቱን እና የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

በአላይደጌና በሌሎች የቱሪዝም መዳረሻዎች የመሰረተ ልማት ማስፋፊያዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው፤ የሰመራ ከተማ የኮሪደር ልማት ቱሪስቶች ወደ ክልሉ ሲመጡ ምቹ ከባቢ ይፈጥራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የክልሉ ከተሞችን ለኑሮ ምቹና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል

ቦንጋ ፣ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከተሞችን ለኑሮ ምቹ፣ ለንግድና ኢንቨስትመንት ተመራጭ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እን...

Oct 29, 2026

የግብርና ልማት ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል

ዱራሜ ፤ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ አሰራርና የተቀናጀ የግብርና ልማት ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥና...

Oct 21, 2026

ኢትዮጵያ እና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በንግድና ኢንቨስትመንት ያላቸው ግንኙነት እያደገ ነው

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በንግድና ኢንቨስትመንት መስክ ያላቸው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን...

Oct 21, 2026

የመደመር መንግስት ለሕዝብ የገባው ቃል ስኬታማ እንዲሆን የድርሻችንን እንወጣለን

ባህር ዳር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግስት በህዝብ ተሳትፎ ስኬታማ ለማድረግ የሚያከናውናቸውን ተግባራት እንደግፋለን ሲሉ የባህር ዳር ከተማ...

Oct 9, 2026