የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የባቡር ሐዲድ

ኢትዮጵያ የአህጉሪቱ የቴክኖሎጂ ማዕከል መሆን የሚያስችላትን ውጤታማ ሥራዎች እያከናወነች ነው

Nov 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የአፍሪካን የሰው ሰራሽ አስተውሎት አቅም በማሳደግ የአህጉሪቱ የቴክኖሎጂ ማዕከል መሆን የሚያስችላትን ውጤታማ ሥራዎች እያከናወነች መሆኑን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ገለጹ።

የፓን አፍሪካ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የንግድ ሥራ ፈጠራ ማበልፀጊያ ስልጠና ፕሮግራም መካሄድ ጀምሯል፡፡


በመርሐ ግብሩ ላይ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ወጣት የዘርፉ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ተገኝተዋል፡፡

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ አጠቃላይ የኢኮኖሚ፣ የጤና፣ የግብርና እና የአስተዳደር ሥርዓቶችን በከፍተኛ ደረጃ በመቀየር ላይ ይገኛል።

ኢትዮጵያ በዚህ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ እንቅስቃሴ ውስጥ ተመልካች ሳትሆን፣ በንቃት በመሳተፍ የራሷን ቴክኖሎጂ የምትገነባበትን ስትራቴጂካዊ ምርጫ ማድረጓንም አብራርተዋል።

የዚህ ራዕይ ቁልፍ ምሰሶ ከሆኑት መካከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የተደረገው የመደመር የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ አንዱ እንደሆነ ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው በ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ የኢትዮጵያን ዲጂታል መሠረተ ልማት፣ የምርምር አቅምና የቴክኖሎጂ ብቃት ለማስፋፋት የተያዘ ስትራቴጂ አካል ሆኖ መቅረቡንና በአሁኑ ወቅት ግንባታው በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡


ዓላማውም የአፍሪካን ቀጣይ ትውልድ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሳይንቲስቶች፣ መሐንዲሶችና የሥራ ፈጣሪዎችን በስፋት ማፈራት እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩትን በማቋቋም ለወደፊቱ የቴክኖሎጂ ዓለም ትልቅ እርምጃ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ተልዕኮ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ምርምርና ልማት ማካሄድ፣ ብሔራዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አቅምና ባለሙያዎችን ማፍራት፣ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ዘርፎች የሰው ሰራሽ አስተውሎት መፍትሔዎችን ማበልጸግ እንዲሁም በፖሊሲ፣ በሥነ ምግባር፣ በመረጃ አስተዳደርና በባለሙያ ልማት ዙሪያ አጠቃላይ ሥራዎችን ማከናወን እንደሆነ አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፖሊሲዋን ይፋ ማድረጓ በአፍሪካ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አስተዳደርና ፈጠራ ዘርፍ መሪ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንድትመደብ እንደሚያደርጋት ተናግረዋል።

ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በኢንስቲትዩቱ ዋና መሥሪያ ቤት የAI Uni Pod ማዕከል መመረቁን አውስተዋል።


ማዕከሉ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂንና ብሔራዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፖሊሲን የሚደግፍ ከመሆኑም በላይ መንግሥትን፣ ተመራማሪዎችን፣ የግል ዘርፉን እና ወጣት ፈጣሪዎችን በአንድ ላይ የሚያሰባስብ ነው።

ዘመናዊ ላቦራቶሪዎችን፣ የሮቦቲክስ መሣሪያዎችን፣ ከፍተኛ የኮምፒውተር ማስላት አቅምን፣ የዲዛይን ስቱዲዮዎችንና የትብብር ትምህርት ቦታዎችን ያካተተው ይህ ማዕከል፤ ምርምር ከሥራ ፈጠራ ጋር የሚገናኝበት፣ ሀሳቦችና የመጀመሪያ ሙከራዎች ወደ ተግባራዊ ምርት የሚቀየሩበት ዋና ስፍራ መሆኑን ገልጸዋል።

አፍሪካ በዓለም ላይ በወጣቶች ቁጥር ከፍተኛ ድርሻ ያላት አህጉር ብትሆንም ማንኛዋም ሀገር የአህጉሪቱን የወደፊት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ጉዞ በብቸኝነት መገንባት እንደማትችል ጠቁመዋል።

በመሆኑም ኢትዮጵያ በጋራና በአንድነት ለመሥራት እየተጋች መሆኗን ገልጸው፣ የአፍሪካ መረጃዎች በአግባቡና በኃላፊነት በአገራት መካከል ሲጋሩ ቴክኖሎጂዎች፣ ቋንቋዎች፣ ባህላዊ አገላለጾች እና ገበያዎች በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ እንደሚያግዙና መሰል የሥራ ፈጠራ ማበልጸጊያ ፕሮግራሞች ወጣቶች ጎን ለጎን እንዲሠሩ ሰፊ ዕድል እንደሚፈጥሩ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የክልሉ ከተሞችን ለኑሮ ምቹና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል

ቦንጋ ፣ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከተሞችን ለኑሮ ምቹ፣ ለንግድና ኢንቨስትመንት ተመራጭ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እን...

Oct 29, 2026

የግብርና ልማት ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል

ዱራሜ ፤ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ አሰራርና የተቀናጀ የግብርና ልማት ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥና...

Oct 21, 2026

ኢትዮጵያ እና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በንግድና ኢንቨስትመንት ያላቸው ግንኙነት እያደገ ነው

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በንግድና ኢንቨስትመንት መስክ ያላቸው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን...

Oct 21, 2026

የመደመር መንግስት ለሕዝብ የገባው ቃል ስኬታማ እንዲሆን የድርሻችንን እንወጣለን

ባህር ዳር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግስት በህዝብ ተሳትፎ ስኬታማ ለማድረግ የሚያከናውናቸውን ተግባራት እንደግፋለን ሲሉ የባህር ዳር ከተማ...

Oct 9, 2026