የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በዞኑ የሰፈነው ሰላም የነዋሪውን የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች ለመመለስ አስችሏል

Jun 26, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጊምቢ፤ ሰኔ 19/2018 (ኢዜአ)፦በምዕራብ ወለጋ ዞን የሰፈነው ሰላም የነዋሪውን የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች ለመመለስ አስችሏል ሲሉ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ገለጹ።

የዞኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች በበጀት ዓመቱ ግንባታቸው የተጠናቀቀ የመሠረተ ልማት ተቋማትን በማስመረቅ ላይ ይገኛሉ።

በዚሁ መሠረት በዞኑ ቆንዳላ ወረዳ ከ219 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የንጹሕ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት የተመረቀ ሲሆን፣ በመንዲ ከተማ አስተዳደር ደግሞ በ42 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ የአስተዳደር ሕንጻ ለአገልግሎት በቅቷል።


በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተሊላ ተረፈ እንደተናገሩት፤ በበጀት ዓመቱ በዞኑ የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብና ጥራት ተጠናቅቀው ለአገልግሎት እየበቁ ነው።

ከእነዚህ የመሠረተ ልማት ተቋማት መካከል በቆንዳላ ወረዳ ለአገልግሎት የበቃው የንጹሕ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት የነዋሪው የረጅም ጊዜ ጥያቄ እንደነበረ ገልጸዋል።

በአካባቢው የነበረው የጸጥታ ችግር መፍትሄ አግኝቶ አስተማማኝ ሰላም በመስፈኑ፣ የመሠረተ ልማት ተቋማቱን ግንባታ ለማፋጠን ትልቅ ዕድል መፍጠሩን አስረድተዋል።


በቀጣይም የተጀመሩ የልማት ሥራዎች የበለጠ እንዲጠናከሩ ሕዝቡ ከምንጊዜውም በላይ የአካባቢውን ሰላም በንቃት መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል።

የዞኑን የሕዝብ የልማት ጥያቄዎች በሂደት በመመለስ፣ የአካባቢውን የልማት አቅም አሟጦ ለመጠቀም እንደሚሠራም አስረድተዋል።

በሕዝቡና በመንግሥት በጀት የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ አስፈላጊው ጥበቃና እንክብካቤ ሊደረግላቸው እንደሚገባም ጠቅሰዋል።

የምዕራብ ወለጋ ዞን ውኃና ኢነርጂ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ቀነኒ በበኩላቸው፤ በበጀት ዓመቱ የንጹሕ መጠጥ ውኃ አቅርቦትን የሚያሳድጉ የውኃ ፕሮጀክቶች ግንባታ ሲካሄድ መቆየቱን ተናግረዋል።


እነዚህ የንጹሕ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች የ116 ሺህ ሰዎችን የንጹሕ መጠጥ ውኃ ችግር ለመፍታት የሚያስችሉ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በተመሳሳይም የመንዲ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ፈቀደ ታሲሳ፣ በከተማው ለአገልግሎት የበቃው የአስተዳደር ሕንፃው በከተማው ውስጥ የተሳለጠና የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጠት ያስችላል ብለዋል።


ሕንጻው 370 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ፣ 28 የተለያዩ የአገልግሎት ክፍሎች ያሉትና በአንድ ጊዜ በርካታ ተገልጋዮችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑን ገልጸዋል።

ከቆንዳላ ወረዳ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ሙፍተሃ የሱፍ በሰጡት አስተያየት፤ ፕሮጀክቱ የረጅም ጊዜ የንጹሕ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ችግራቸውን እንደሚያቃልልላቸው ተናግረዋል።


በአካባቢው ንጹሕ የመጠጥ ውኃ ለማግኘት ረጅም ርቀት በእግር መጓዝ ግዴታቸው እንደነበር አስታውሰው፣ ከዚህ ቀደም በነበረው የንጹሕ ውኃ አቅርቦት እጥረት ሳቢያ ለተለያዩ የውኃ ወለድ በሽታዎች ተጋልጠው መቆየታቸውንም ገልጸዋል።


ሌላኛዋ የወረዳው ነዋሪ ወይዘሮ ሾኔ ሻፊ በበኩላቸው፤ አሁን ላይ ጥያቄያቸው ምላሽ በማግኘቱ መደሰታቸውን ተናግረዋል።

መንግሥት የሕዝቡን የመሠረተ ልማት ፍላጎት ጥያቄዎች ለመመለስ እያደረገ ያለውን ጥረት ያደነቁት ነዋሪዋ፤ ለአገልግሎት የበቃው ይህ የንጹሕ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ረጅም ዕድሜ እንዲያገለግል ተገቢውን ጥበቃና እንክብካቤ በማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026