የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

ሀገር አቀፍ የህብረት ሥራ ስትራቴጂ እና ፍኖተ ካርታ የማህበራትን አሠራር ዘመናዊ በማድረግ ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው

Jun 27, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19/2018 (ኢዜአ)፦ አዲሱ ሀገር አቀፍ የህብረት ሥራ ስትራቴጂ እና ፍኖተ ካርታ የህብረት ሥራ ማህበራትን አሠራር ዘመናዊ በማድረግ ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር መሆኑን የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ ገለጹ።

የግብርና ሚኒስቴር የአስር ዓመት ሀገር አቀፍ የህብረት ሥራ ስትራቴጂ እና ፍኖተ ካርታ የንቅናቄ መድረክ ማካሄድ ጀምሯል።


የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ አዲሱ ፍኖተ ካርታ የህብረት ሥራ ማህበራትን አሠራር ዘመናዊ በማድረግ ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው።

ማህበራቱን በስፋት በማደራጀትና ተወዳዳሪነታቸውን በማሳደግ የገጠርና የከተማ ትስስርን ማጠናከር እንደሚቻል ገልጸው፣ ይህም ኢትዮጵያ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ለማረጋገጥ ትልቅ አቅም እንደሚሆን ጠቁመዋል።

ስትራቴጂውና ፍኖተ ካርታው በዋናነት በርካታ ጠቀሜታዎችን እንደሚያስገኝ ጠቁመው የግብርና ሽግግርን በማፋጠን፣ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሩንና የአርብቶ አደሩን የኑሮ ደረጃ ከፍ ያደርጋል ብለዋል።

በተጨማሪም የህብረት ሥራ ማህበራትን የሚያዘምን መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ የህብረት ሥራን ማዘመን ግብርናን ማዘመን ነው፤ግብርናን ማዘመን ደግሞ የሀገርን ኢኮኖሚ ማረጋገጥ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።


ከዚህ ቀደም በህብረት ሥራ ማህበራት ውስጥ ሲያጋጥሙ የነበሩ መዋቅራዊና አሠራራዊ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ ያስችላልም ብለዋል፡፡

ስትራቴጂው ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር ሲገባ ምርትና ምርታማነትን በማረጋገጥ ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሪ እንደሚያስገኝም ጠቁመዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት ከፍ የሚያድርግ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ይህ አገር አቀፍ የአስር ዓመት ስትራቴጂና ፍኖተ ካርታ የግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚን በማፋጠን፣ ማህበራቱ በሀገር ውስጥ ምርት ሥርጭትና በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ የጎላ እንደሚያደርገው በንቅናቄ መድረኩ ላይ ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026