የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

ኢትዮጵያ ከዩናይትድ ኪንግደም ጋር የዓለም ንግድ ድርጅት የሁለትዮሽ ገበያ ዕድል ስምምነት ተፈራረመች

Aug 21, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ ፤ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ)፦​ኢትዮጵያ ከዩናይትድ ኪንግደም ጋር በዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) አባልነት ሂደት ማዕቀፍ ስታካሂድ የቆየችውን የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድር በስኬት በማጠናቀቅ የስምምነት ሰነድ ተፈራርማለች።

​የስምምነት ሰነዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ዋና ተደራዳሪ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር እና በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደር ዳረን ዌልች ተፈራርመውታል።

​በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ይህ ታሪካዊ ስምምነት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም እና የፖሊሲ ምህዳር ሙሉ በሙሉ ባስጠበቀ መልኩ የተከናወነ ነው ብለዋል።

አክለውም ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት የቆየ ዲፕሎማሲያዊ፣ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር ከመሆኑም በላይ፣ ኢትዮጵያ በዓለም ንግድ ድርጅት ሙሉ አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ ወሳኝ ስኬት መሆኑን አብራርተዋል።

የዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደር ዳረን ዌልች በበኩላቸው፤ የተደረገው ስምምነት የሁለቱን ሀገራት የቆየ የኢኮኖሚና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጎለብት መሆኑን ገልጸዋል።

ዩናይትድ ኪንግደም ኢትዮጵያ ወደ ዓለም ንግድ ድርጅት ለመቀላቀል የምታደርገውን ጥረት እና የምታካሂዳቸውን የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በሙሉ ቁርጠኝነት መደገፏን የምትቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።

​ኢትዮጵያ እስካሁን ባለው ሂደት ከቻይና፣ ሩሲያ፣ አርጀንቲና፣ ቱርክ፣ ብራዚል፣ ጃፓን፣ ሕንድ፣ ኒውዚላንድ እና ታይላንድ ጋር ተመሳሳይ ስምምነቶችን ተፈራርማለች።

ዩናይትድ ኪንግደም ስምምነቱን በይፋ ከፈረሙ አባል ሀገራት 10ኛዋ እና ድርድሩን በስኬት ካጠናቀቁት ደግሞ 11ኛዋ አባል ሀገር ሆናለች።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ዘላቂ ተጠቃሚነታችንን ለማረጋገጥ አስችሎናል-አርሶ አደሮች

ደብረብርሃን፤ ነሀሴ 14/2018 (ኢዜአ)፡-በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በመሳተፍ ዘላቂ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ መቻላቸውን አርሶ አደሮች ገለጹ። የሌማት ት...

Aug 21, 2026

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ከማዕድን ተገቢው ገቢ እንዲገኝ በትምህርት፣ በምርምር እና በአቅም ግንባታ ዘርፍ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ከማዕድን ተገቢውን ገቢ እንድታገኝ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት፣ በምርምር እና በአቅም ግንባታ ዘርፍ የ...

Aug 18, 2026

በክልሉ ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ወደ ሥራ ገብተዋል

ሚዛን አማን፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በ2018 በጀት ዓመት ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ፈቃድ...

Aug 14, 2026

ፓርኩን በማልማትና በመጠበቅ ዘላቂ የገቢ ምንጭ ለማድረግ ቅንጅታዊ ሥራን ማጠናከር ይገባል 

ሮቤ ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን በማልማትና በመጠበቅ ዘላቂ የገቢ ምንጭ ለማድረግ በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ የኢትዮጵያ ዱር...

Aug 7, 2026