የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የመደመር መንግሥት የኦዲት ግኝቶችን በግብዓትነት በመጠቀም ግልጽ የፋይናንስ ሥርዓት እየተከተለ ነው

Oct 21, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት የኦዲት ግኝቶችን በግብዓትነት በመጠቀም በተሞክሮነት የሚወሰድ ግልጽ የፋይናንስ ሥርዓት እየተከተለ መሆኑን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሰረት ዳምጤ ገለጹ።

የኢፌዴሪ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤትና ዓለም አቀፍ የከፍተኛ ኦዲት ተቋማት ድርጅት ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የአፍሪካ ክልላዊ የከፍተኛ ኦዲት ተቋማት ውጤታማነትን ለማጠናከር የተዘረጋውን ተነሳሽነት የአፈጻጸምና የፕሮጀክት አስተዳደር ክትትል አቅም ለማጠናከር ያለመ ስልጠና መካሄድ ጀምሯል።


በአዲስ አበባ ከተማ ለሶስት ቀናት በሚቆየው አውደ ጥናት የፕሮጀክት አስተዳደር፣ የትብብርና የክትትል አቅም ግንባታን ማሳደግ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተመልክቷል።

የአፍሪካ ክልላዊ የከፍተኛ ኦዲት ተቋማት ውጤታማነትን ለማጠናከር የተዘረጋው ተነሳሽነት በኢንቶሳይ የልማት ተነሳሽነትና በኖርዌይ የልማት ትብብር ኤጀንሲ ድጋፍ ከ2025 እስከ 2028 ድረስ እየተተገበረ ይገኛል።

መርሃ ግብሩ የአፍሪካ ከፍተኛ የኦዲት ተቋማት የረጅም ጊዜ ድጋፍ በመስጠት ተቋማዊ አቅማቸውን ማሳደግ፣ የኦዲት ጥራትን ማሻሻል፣ ተጠያቂነትንና የበጀት አስተዳደርን ማጠናከር ያለመ ነው።

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሰረት ዳምጤ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል ከመሆኗ በተጨማሪ በአዲስ አበባ የተከናወነው ዘመኑን የዋጀ ለውጥ ከተማዋን ለስልጠናው ተመራጭ አድርጓታል።

በአዲስ አበባ በአጭር ጊዜ የተከናወኑ የመሰረተ ልማት፣ የትራንስፖርት፣ የህዝብ መዝናኛና የአረንጓዴ ስፍራዎች ልማት የዜጎችን ህይወት በማሻሻል ከፍተኛ ጠቀሜታ እያበረከቱ መሆኑን አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች በመደመር ፍልስፍናና ጠንካራ ሀገር የመገንባት ርዕይ መሰረት የሚከናወኑ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫና የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በመጠቆም፤ ለአህጉራዊ ትብብርና ዕድገት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተች የምትገኝ ከተማ መሆኗን አንስተዋል።


የአፍሪካ የኦዲት ተቋማትን አቅም ለማጠናከር የተዘጋጀው አህጉራዊ አውደ ጥናት የጋራ ልምድና ተሞክሮን ለመጋራት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረውም ገልጸዋል።

ስልጠናው የአባል ሀገራትን የኦዲት ትብብር በማጠናከር ልምድና ተሞክሮ የሚለዋወጡበት መድረክ ሲሆን፤ የኦዲት ስራን በውጤታማነት ለማከናወን የሚያስችሉ እውቀቶችንና ክህሎቶችን ለመጋራትም ያግዛል ብለዋል።

በዚህም አፍሪካዊያን በመካከላቸው ያለውን ልምድና ተሞክሮ በመለዋወጥ ጥራትንና ውጤታማነትን ያጣመረ ጠንካራ የኦዲት ስርዓት መገንባት ይጠበቅብናል ብለዋል።

ዋና ኦዲተሯ አያይዘው የመደመር መንግሥት በአሁኑ ወቅት የኦዲት ግኝቶችን እንደ ግብዓት በመጠቀም ከኦዲት ግኝት ጋር በተገናኘ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያደርገው ጥረት የሚበረታታ ነው ብለዋል።

በተለይም በኦዲት ግኝቶች መሰረት በተቋማት የሚስተዋሉ ህጋዊ ያልሆኑ ድርጊቶችን ወደ ትክክለኛው መስመር ለማስገባት የተጠያቂነት አሰራርን እየዘረጋ መሆኑን ጠቅሰው፤ የሀገርና የህዝብ ሀብት እንዲመለስ የሚሄድበት ርቀት እንደሚደነቅ ተናግረዋል።

የኦዲት ስራን በቴክኖሎጂ በተደገፈ መንገድ ለማስኬድ የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡


የዓለም አቀፍ የከፍተኛ ኦዲት ተቋማት የልማት ተነሳሽነት የሁለትዮሽ ድጋፍ ክፍል ከፍተኛ ስራ አስኪያጅ መሐመድ ዳቦ በበኩላቸው፤ ስልጠናው የአፍሪካ ቀጣናዊ ከፍተኛ የኦዲት ተቋማትን ውጤታማነት ለማሳደግ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ለሶስት ቀናት የሚቆየው ስልጠና የአባል ሀገራት ተቋማት የሙያ ልምድና ተሞክሮ በመጋራት ለቀጣይ ተልዕኮዎቻቸው ተጨማሪ አቅም እንዲፈጥሩ የሚያግዝ መሆኑንም አስረድተዋል።

ስልጠናው በኦዲት ስራ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ያማከሉ መፍትሄ አመንጪ ምክረ ሀሳቦችን ለማዘጋጀት እንደሚረዳም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ወደ ሥራ መግባት የአካባቢውን ቱሪዝም ከማነቃቃት ባለፈ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ አድርጎናል

ጎንደር ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ወደ ሥራ መግባት የአካባቢውን ቱሪዝም ከማነቃቃት ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ አድርጎናል ሲሉ የአካ...

Oct 20, 2026

ኢትዮጵያ እና አይኤምኤፍ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ትብብራቸውን ማጠናከር ያለመ የሁለትዮሽ ምክክር አድርገዋ...

Oct 13, 2026

ቀደም ሲል ችላ የተባለው የማዕድን ዘርፍ፣ ዛሬ የዕድገት ስትራቴጂካዊ ሞተር ሆኗል!

ቀደም ሲል ችላ የተባለው የማዕድን ዘርፍ፣ ዛሬ የዕድገት ስትራቴጂካዊ ሞተር ሆኗል! በ#መደመርመንግሥት አማካኝነት የማዕድን ዘርፉ አቅሙን በማላቅ ለኢኮኖሚ ለውጥ...

Oct 13, 2026

ኮደርስ ኢንሼቲቭ የዜጎችን ዲጂታል ክህሎት በማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮ-ኮደርስ ኢንሼቲቭ የዜጎችን ዲጂታል ክህሎት በማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ የኢኖቬሽንና ቴክ...

Oct 4, 2026