የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

ኢትዮጵያ እና አይኤምኤፍ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ

Oct 13, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ትብብራቸውን ማጠናከር ያለመ የሁለትዮሽ ምክክር አድርገዋል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተመራ ልዑካን ቡድን በታይላንድ ባንኮክ ዛሬ በተጀመረው የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከስብስባው ጎን ለጎን ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የአፍሪካ ክፍል ዳይሬክተር ዘይን ዘይዳን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።


ውይይቱ በኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ ላይ ያተኮረ ነው።

ምክክሩ እስካሁን በሪፎርሙ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለመገምገም፣ የቅርብ ጊዜ የኢኮኖሚ ሁኔታዎችን ለመዳሰስ እና በቀጣይ በሚተገበሩ የሪፎርም ስራዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ለመለየት ማስቻሉ ተመላክቷል።

ሁለቱ ወገኖች የማክሮ ኢኮኖሚ ዘላቂነትን በማጠናከር ለአካታችና ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት የሚያስፈልጉ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ቀደም ሲል ችላ የተባለው የማዕድን ዘርፍ፣ ዛሬ የዕድገት ስትራቴጂካዊ ሞተር ሆኗል!

ቀደም ሲል ችላ የተባለው የማዕድን ዘርፍ፣ ዛሬ የዕድገት ስትራቴጂካዊ ሞተር ሆኗል! በ#መደመርመንግሥት አማካኝነት የማዕድን ዘርፉ አቅሙን በማላቅ ለኢኮኖሚ ለውጥ...

Oct 13, 2026

ኢትዮጵያ እና አይኤምኤፍ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ትብብራቸውን ማጠናከር ያለመ የሁለትዮሽ ምክክር አድርገዋ...

Oct 13, 2026

ኮደርስ ኢንሼቲቭ የዜጎችን ዲጂታል ክህሎት በማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮ-ኮደርስ ኢንሼቲቭ የዜጎችን ዲጂታል ክህሎት በማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ የኢኖቬሽንና ቴክ...

Oct 4, 2026

የኢትዮ-ጅቡቲ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክት የሀገራቱንና የቀጣናውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ያጠናክራል- ምሁራን

አዲስ አበባ፤ መስከረም 16/2019 (ኢዜአ)፦ በጅቡቲ ዳመርጆግና በኢትዮጵያ ደወሌ መካከል የሚዘረጋው የ120 ኪሎ ሜትር የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክት የ...

Sep 28, 2026